አንቺ ባለ ጋሜ እስኪ ልበሽ ካባሽን
መድረኩ ያንቺ ብቻ ትከሻሽን አሳዩን
ክሽን ባለችዋ እስክስታሽ አስደምሚን
ዘመድ አዝማዱ መንገደኛ ሚጠብቀው አንቺን
ታድያ የምን የምን የምን ወደዃላ
ወዲ ነይ ሸጊቱ እንዳይሉብኝ አንቺን ቀብራራ
እኔም እንዳልወቀስብሽ በውሸት ፉከራ
ሳወድስሽ ቆይቼ ለህዝቡ ብቻዬን ብወጣ
ዴ! በል አንዴ ሀበሻዊ
ለእስክስታ ለዝማሬ
ለዳንኪራ ውዝዋዜ
ሲግደረደር አይተን እናውቃለን እንዴ! (ኤኤኤ)
እንቆቅልሽ ሆነሻል እቱ!
ወጉን ይዘሽው ምንድነው ታዲያ አኩኩሉ
ሚሉትን ቢሉ አወቅን ብለው ቢራቀቁ
ትከሻሽ ሲናገር ሙያሽን እያሉ ያዜማሉ
ወዲ ነይ ወዲ ነይ
የምን ወዲያ ወዲያ
ካገሬ ልጅ ጋራ (ትከሻሽን)
አርጊው መታ መታ (አርጊው መታ መታ)
(አርጊው መታ መታ)
(Flashkiiddo on the track)
እኔስ እጅ ነሳሁና በባህሏ ፍቅር
አፈኘችውን ጉድ አስባለች ሰምታ የኔን ምክር
ልቅም ያለች ትከሻዋን ስትሰካ ስትሰብር
እንደ ደነዘዝን በላያችን ትተካብን ጀመር
ጉድ እኮ ነው የምትጠቀመው ቀምር
ጥርሷን ነክሳ ለከበቧት ወጉን ስታስተምር
አጋፋሪዋ ኑ ሹክ በለኝ የሷን ምስጢር
እኔም ታድያ ጠጋ ብዬ ሁሉን አፍረጥርጬ ንግር
ትከሻ በጐጃም ጥበብ ተገርቶ
ጐንደር ሄዶ በጀግና ጀግናዎቹ ተከሽኖ
ሸገርን ሊያተራምስ ከተፍ አለ ተንደርድሮ
አሁን ታዲያ ማን ይቻላል ብልጠቷን ለቀበሮ
(እሷ)
አትቀመስ ቢቻል እንኳን ወገብ ተበድሮ (ሊያውም)
ላንቺ ነዋ ገደብ የለው ሲመታ ከበሮ (ታድያ)
ሃይሎጋ ብለን እናጅባት ኢቺን መለሎ
ማድነቁ ይበጀናል መፎጋገርስ ቀረ ድሮ
ወዲ ነይ ወዲ ነይ
የምን ወዲያ ወዲያ (ወይ ወይ ወይ)
ካገሬ ልጅ ጋራ (ትከሻሽን)
አርጊው መታ መታ (አርጊው እስቲ)
ወዲ ነይ ወዲ ነይ (አርጊው መታ)
የምን ወዲያ ወዲያ(መታ መታ)
ያገሬ ልጅ ጋራ(ትከሻሽን)
(አርጊው መታ መታ)
(አርጊው መታ)
(አርጊው እስቲ)
(ትከሻሽን)
(Flashkiiddo on the track boy)
(እስኪ ምችው)
(አርጊው እስቲ)
(ትከሻሽን)
(አርጊው መታ መታ)
(አርጊው መታ)
(አርጊው እስቲ)
(ትከሻሽን)
(አርጊው መታ መታ)
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist