Yared Negu - Hulum Hagere lyrics
Artist:
Yared Negu
album: Hulum Hagere
ያሬድ ነጉ
ከጉራጌ ባወጣኝ እግሬ
ከመርካቶ ጎጃም በርሬ
የትም ብሄድ ሁሉም ሀገሬ
ለፍቶ አዳሪ ጠንካራ ዘሬ
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
አለመድሽኝና አስከ ጥግ ድረስ
ቀረው ሳልመለስ
ያውቅበታል ጎጃም እንዳባይ ማስመጡን
ፍቅር ማጣፈጡን
ብደክም ብለፋ መች ይሰለቸኛል
መለኛው ጎጃሜ ማኛውን ሰቶኛል
መቼም አይታማ ጉራጌ ለስራ
ጎጃምም አላጣም ፍቅርና እንጀራ
እንጀራም እንጀራ ፍቅርም ሀገር የለው
አቤት ሲያገጣጥም እህል ውሀ እንዲህ ነው
የሰርጋችን ድግስ ጎጃም ላይ ከሆነ
ተመታ መሬቱ አቧራው ቦነነ
አንተዬ እስቲ ባህልህን ልየው ጭፈራህን
ላሳይሽ
አንቺዬ ጎጃሜነትሺ
ያምራል ትከሻሺ
ከጉራጌ ባወጣኝ እግሬ
ከመርካቶ ጎጃም በርሬ
የትም ብሄድ ሁሉም ሀገሬ
ለፍቶ አዳሪ ጠንካራ ዘሬ
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
ለፍቶ አዳሪው ልቤ ማርዬን አግኝቶ
ቀረ ጎጃም ገብቶ
በዘፈን በዝና የሰማሁት ሁሉ
ለጎጃም ያንሳሉ
ብደክም ብለፋ መች ይሰለቸኛል
መለኛው ጎጃሜ ማኛውን ሰቶኛል
መቼም አይታማ ጉራጌ ለስራ
ጎጃምም አላጣም ፍቅርና እንጀራ
እንጀራም እንጀራ ፍቅርም ሀገር የለው
አቤት ሲያገጣጥም እህል ውሀ እንዲህ ነው
የሰርጋችን ድግስ ጎጃም ላይ ከሆነ
ተመታ መሬቱ አቧራው ቦነነ
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist