Kishore Kumar Hits

Ahadu - Digis lyrics

Artist: Ahadu

album: Digis


አሐዱ
ከሩቅ ይጣራል የጀግናው ፈረስ
ድልን አሳክቶ ደረሰ ከቤት
ግርማውን አይቷል ይመስክር ጠላት
እምነት የጫረው የያዘው እሳት
ከፊት የሚቀድመው አባ ኮስትር
በላይ የኢትዮጵያ ልጅ ሞተ ለእውነት
ድሮስ መተውበት በእናት ባገር
ቁጭት ህመሙ አቀዳጀው ድል
ድግስ
አለ ድግስ
እንኳን ለሹማመንት አለ ለምርኮኛ እራት
ነካክተውን እንጂ ወትሮም አናውቅም ክፋት
ለነከሰው ቢያጎርስ አስተማረው ፍቅርን
ድግስ
አለ ድግስ
እንኳን ለሹማመንት አለ ለምርኮኛ እራት
ድግስ
አለ ድግስ
እንኳን ለሹማመንት አለ ለምርኮኛ እራት
ድግስ
አለ ድግስ
እንኳን ለሹማመንት አለ ለምርኮኛ እራት
ድግስ
አለ ድግስ
እንኳን ለሹማመንት አለ ለምርኮኛ እራት
አለው የደስ ደስ አለው የደስ ደስ
የዋዜማው ለታ ሲባል ሽር ጉድ
ይጠመቃል አሉ ግሩም የወይን ጠጅ
እንኳን ሎሌ ቀርቶ ንጉሥ የሚያስጎመጅ
ዘመናት ቆየ ጣፋጭ እንዲሆን
አጋፋሪው ይላል ሙያን ሲያወድስ
ሽቅብ እየወጣ ይታያል ሲሄድ
እንስራ ሲታጠን በወይራ ጢስ
እልልታው ካሁኑ ደመቀ አየለብኝ
በዚህ ከቀጠለ የሌቱን እንጃልኝ
ተሰናድቷል አሉ ሰታቴው ከቤቱ
ሆድ ይክዳል እንጂ አያንስም ሌማቱ
ድግስ
አለ ድግስ
እንኳን ለሹማመንት አለ ለምርኮኛ እራት
ነካክተውን እንጂ ወትሮም አናውቅም ክፋት
ለነከሰው ቢያጎርስ አስተማረው ፍቅርን
ድግስ
አለ ድግስ
እንኳን ለሹማመንት አለ ለምርኮኛ እራት
ድግስ
አለ ድግስ
እንኳን ለሹማመንት አለ ለምርኮኛ እራት
ድግስ
አለ ድግስ
እንኳን ለሹማመንት አለ ለምርኮኛ እራት
ድግስ
አለ ድግስ
እንኳን ለሹማመንት አለ ለምርኮኛ እራት
ኧረ ጎበዝ ኧረ ጎበዝ
ሞላው እልልታ አቤት ሞገሱ
ያገሬ ልጆች ቦታው ደረሱ
ሞቅ አርገው ሞቅ
ሞቅ አርጊው ሞቅ
ወገብሽን ጠበቅ
በይ እንዳትለቂ
እያሀ ያመናል በለው
እያሃ ያመናል በለው
እያሀ ያመናል በለው
እያሃ ያመናል በለው
ኧረ ጎበዝ ኧረ ጎበዝ
አንዱ ምሰሶ አንዱ ማግር
አንዱ ቢጎድል ቤት አይፀናም
ቤት አይፀናም
ቤት አይፀናም
ቤት አይፀናም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists