አሃዱ
የጀግና ዘር የገበሬው
ያድዋ አርበኛው የማይጨው
'ማይሸበር ኧረ የማይተኛው
ከክብሩ አንገቱን ቀድሞ ለሰጠው
በእውቀት ጥልቀት ለበቃው
የነበር ያውቃል የሚይውቀው
ከጥበብ ምጥቀት ከፀጋ ንብረት
በእውነት ለመኖር ሲባል በህብረት
እናቱ ጀግና
አንድ ላይ ዘማች ቆራጥ ናት ለወገን 'ምትደርሰው
እህ ያ ምስኪን
ካንጀቱ ቀንሶ አዎን ለሰው የሚያጎርሰው
መሰረት ለሰው ዘር የጥንቱም ገናና
ሁሌም ጥንትም ያ ጎበዝ ጀግና
ያሆ ያሆ
ላላይ ጉማ ጥንትም ነው ጀግና
አሃ ሀይ ጉማ
ላላይ ጉማ ስር መሰረቱ
አሃ ሀይ ጉማ
ላላይ ጉማ ቆራጥ ናት ሴቷም
አሃ ሀይ ጉማ
ላላይ ጉማ ደራሽ ለቤቷም
አሃ ሀይ ጉማ
ላላይ ጉማ ኣሃሃ
ላላይ ጉማ አሃሃ
ያደፋሩ አሃሃ
ሙሉ ክብሩ አሃሃ
ጀግና አንበሳ አሃሃ
ለሃገሩ አሃሃ
ላላይ ጉማ አሃሃ
ላላይ ጉማ አሃሃ
እህህህ ጎራው ና
እህህህ ጎራው ና
እህህህ ጎራው ና (ጎራው ጎራው ጎራው ና)
ያ ንቁ ገበሬ የጀግና ዘር ግንዱ
የልቡን ሳያደርስ አይገባ ከቤቱ
ከልፋቱ ክብሩን ከራሱ ሀገሩን
አስቀድሞ ሟች ነው ለ'ምዬ ለእናቱ
ዝናር ከወገቡ ምንሽርን በጁ
ጀግና የጀግና ልጅ ወንድ ነው እንዳባቱ
ከፊቱ ይታያል ኩራቱ
በልቡ የዋህ ነው ደምግባተ ሙሉ
ቢርቅም እግሬ ካገር መንደሬ
ልቤ ናፍቆሽ አንቺን ቢልም
የሰው ሀገር ምን ቢመቸኝም
ያላንቺ እንኳን አይሆነኝም
አንቺ 'ኮ ነሽ ያ ፅኑ ሃሳቤ
ውሎ አዳርሽ እንዴት ነው ሀገሬ
ቢሳካልኝ እቅድ ውጥኔ
ብመጣልሽ እናት ሀገሬ
ጎበዝ የሀገርል ልጅ መች ቸግሯት ያውቃል
ፍቅር አለ ከቤቷ መርቆ አድሏታል
ይታያል ግንባሯ ወትሮም ያስታውቃል
ከነኳት ነው እንጂ ካልነኳት አትነካም
በናቱም ባባቱም አርበኛ
ጀግና የወለደው ቀበኛ
ቀዳሚ ስሙ ገናና
ሁሌም ጥንትም ያ ጎበዝ ጀግና
ያሆ ያሆ
ላላይ ጉማ ጥንትም ነው ጀግና
አሃ ሀይ ጉማ
ላላይ ጉማ ስር መሰረቱ
አሃ ሀይ ጉማ
ላላይ ጉማ ቆራጥ ናት ሴቷም
አሃ ሀይ ጉማ
ላላይ ጉማ ደራሽ ለቤቷም
አሃ ሀይ ጉማ
ላላይ ጉማ አሃሃ
ላላይ ጉማ አሃሃ
ያደፋሩ አሃሃ
ሙሉ ክብሩ አሃሃ
ጀግና አንበሳ አሃሃ
ለሃገሩ አሃሃ
ላላይ ጉማ አሃሃ
ላላይ ጉማ አሃሃ
አሃሃ
አሃሃ
አሃሃ
አሃሃ
አሃሃ
አሃሃ
አሃሃ
አሃሃ
እኔክሽ እኔካ
እኔክሽ እኔካ
እኔክሽ እኔካ
እኔክሽ እኔካ
እኔክሽ እኔካ
እኔክሽ እኔካ
እኔክሽ እኔካ
እኔክሽ እኔካ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist