Kishore Kumar Hits

Ahadu - Asina Genaye lyrics

Artist: Ahadu

album: Asina Genaye


አሐዱ
አብዬም ተነሱ በሉን የጌቶቹ ጌታ
በረከት የሆኑኝ ፍቅር የማታ ማታ
ጎዶሎ የማያውቁ ደግሞ ሁሌም ጎተራቸው
ስንቱን ያጠገበው ደግሞ ሙሉ መሶባቸው
ከሸራ አልፎ ሙላቱ ከስንዴ ክምሩ
መቼም ላይጎላቸው ሙሉ ነው መንደሩ
እምዬም ብቅ በይ ደግሞ ካገር ጥበብሽ
የእጅ ወርቅሽ ያጎላው ደግሞ ያምራል ጥለትሽ
ሸብ ያለው መቀነቱ ከወገብሽ ያለው
ሁሉን ቻይ አንጀትሽ ስንቱን የሚችለው
አውዳመቱ ደርሶ ሲባል አሲና ገናዬ
ደጅሽ እመጣለው ደግሞ ጠብቂኝ ሸግዬ
አሲና በል አሲና ገናዬ
ኢዮሃ አሲና በል
ኢዮሃ አሲና ገናዬ
አሲና በል በገና ጨዋታ
ኢዮሃ አሲና በል
ኢዮሃ አሲና ገናዬ
አለን ውብ ባህል
'ሚበቃ ለዓለም የማይል ዘር ቀለም
መጥተዋል አዎ ወደው
የአውዳመቱን ድባብ ፈዘው ነው የሚያዩ
ሀብታም ደሃ ፈቅዶ ሲረዳዳ
ደጁ ሁሌ ቅን ዘመድ ይምጣ ባዳ
ጠላውም ቀርቧል ጠጁም ከገበታ
ዶሮ በጉ ሁሉ የጣዕሙ ትዝታ
በዓል በዓል የላል ይሸታል
መንደሩም ሰላም ያኮራል
መጫወት ካገር ልጅ ጋር ደስ ይላል
ወተናል ወርደናል
አጥተን አግኝተን ተመስገን ብለን
ይኸው ለዛሬ ቀን ደርሰናል
እንኳን አደረሳችሁ
እንኳን አብሮ አደረሰን
እንዲሁ እንዳገናኝን
ካመት ዓመት አይለየን
አሲና በል ገናዬ
አሲና በል እንበል
አሲና በል አሲና ገናዬ
ከናት ካባቴ ቤት ያለኝ ትዝታ
እኅት ወንድሞቼ ደስ የሚል ጨዋታ
ጠራኝ የጠዋቱ ጤዛ የበረቱ ሽታ
የእምዬ ጉድ ጉድ የአባብዬ ደስታ
ያለንን ተካፍለን
በፍፁም ቅንነት
ዘመድ አዝማዱም
ሁሉም በያለበት
ሲያከብረው ይኖራል
በሚያምር ኅብረዜማ
በአባቶቻችን ቃል
እያልን እዮሃ
(እልልልል)
አሲና በል አሲና ገናዬ
ኢዮሃ አሲና በል
ኢዮሃ አሲና ገናዬ
አሲና በል በገና ጨዋታ
ኢዮሃ አሲና በል
ኢዮሃ አሲና ገናዬ
ኢዮሃ ኢዮሃ
ኢዮሃ ኢዮሃ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists