Kishore Kumar Hits

Azeb Hailu - በመጀመርያ lyrics

Artist: Azeb Hailu

album: በመጀመርያ እግዚአብሔር


የእግዚያብሔር ፡ ግርማ ፡ ክብርና ፡ ሞገሱ
በፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ታይቶ ፡ ያወራል ፡ ስለእርሱ
ፍቅሩ ፡ ርህራሄው ፡ ቸርነት ፡ ምሕረቱ
ሁሉም ፡ ይዘምራል ፡ በዜማ ፡ አንደበቱ
ሁሉን ፡ ቻይነቱ
ሳይሆን ፡ ገና ፡ ሰማይ ፡ ሳይሆን ፡ ገና ፡ ምድር
መጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር
በላይ ፡ እና ፡ በታች ፡ የሚባል ፡ ሳይኖር
አስቀድሞ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር
ሳትታይ ፡ ጨረቃ ፡ ሳትበራ ፡ ፀሐይ
እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ቀድሞ ፡ አልነበረ ፡ ወይ
ጥዋት ፡ እና ፡ ማታ ፡ ተብሎም ፡ ሳይለይ
በሥልጣን ፡ በክብር ፡ እርሱ ፡ አልነበር ፡ ወይ
አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ በመጀመሪያ
በመጀመሪያ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ በመጀመሪያ
ከሁሉ ፡ በፊት ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁሉ ፡ በላይ
ነበር ፡ እርሱ ፡ መጀመሪያ ፡ ሃሌሉያ (፪x)
ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚኖረው
ሕያው ፡ አምላክ ፡ ልዑል ፡ እግዚአብሔር
የሰራችሁ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ
በመገዛት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉ (፪x)
የውሃው ፡ ክምችት ፡ ሳይባል ፡ ባሕር
መጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር
ምድርም ፡ ሳታበቅ ፡ ቡቃያና ፡ ሳር
አስቀድሞ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር
ሳይለዩ ፡ ገና ፡ ውሃና ፡ መሬቱ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በኃይል ፡ በችሎቱ
እለታት ፡ ዓመታት ፡ ዘመናት ፡ ሳይሆኑ
እርሱ ፡ እንዳለ ፡ አለ ፡ በክብር ፡ ዙፋኑ
አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ በመጀመሪያ
በመጀመሪያ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ በመጀመሪያ
ከሁሉ ፡ በፊት ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁሉ ፡ በላይ
ነበር ፡ እርሱ ፡ መጀመሪያ ፡ ሃሌሉያ (፪x)
ሳይሰራ ፡ አዳም ፡ ሳትመጣ ፡ ሄዋን
መጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር
እፍ ፡ ሳይልበት ፡ ገና ፡ እስትንፋሱን
አስቀድሞ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር
ሳይባሉ ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ እና ፡ ተባዙ
ምድርን ፡ አስተዳድሩ ፡ ፍጥረታትን ፡ ግዙ
አዳም ፡ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ሳይመላለስ
በማደሪያው ፡ አለ ፡ የክብር ፡ ንጉሥ
ስሙም ፡ ቅዱስ
አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ በመጀመሪያ
በመጀመሪያ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ በመጀመሪያ
ከሁሉ ፡ በፊት ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁሉ ፡ በላይ
ነበር ፡ እርሱ ፡ መጀመሪያ ፡ ሃሌሉያ (፪x)
ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚኖረው
ሕያው ፡ አምላክ ፡ ልዑል ፡ እግዚአብሔር
የሰራችሁ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ
በመገዛት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists