Kishore Kumar Hits

Azeb Hailu - በዙፋኑ ላይ lyrics

Artist: Azeb Hailu

album: በመጀመርያ እግዚአብሔር


በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ በማደሪያው ፡ ላይ
በክብርና ፡ በግርማው
ሳይለዋወጥ ፡ ሳይነዋወጥ
እንዲሁ ፡ እንደጵና ፡ ያለው
ከነችሎቱ ፡ ከነብርታቱ ፡ የሚኖረው
ኧረ ፡ ይሄ ፡ ማነው
የአማልክት ፡ አምላክ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡
እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ነው
እግሮቹ ፡ በደመናት ፡ ላይ ፡ ይራመዳሉ
ዓይኖቹ ፡ በምድር ፡ ዙሪያ ፡ ሁሉ ፡ ያያሉ
አይገለጥም ፡ በቋንቋ ፡ ታላቅነቱ
እኔ ፡ ክብር ፡ እሰጣለው ፡ ለጌትነቱ
አይገለጥም ፡ በቋንቋ ፡ ታላቅነቱ
እኔ ፡ ስግደት ፡ አበዛለው ፡ ለጌትነቱ
ፍጥረት ፡ የሚሰማው ፡ የሚወደው
ገና ፡ ሳይነጋ ፡ በማለዳው
እግዚአብዜር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ
የሚለውን ፡ ቃል ፡ በመሆኑ
እኔም ፡ ልዘምር ፡ ይህንኑ
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ
እኔም ፡ ልዘምር ፡ ይህንኑ
አምላኬ ፡ አለ ፡ በዙፋኑ
በክብር ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ከብሯል
በኃይል ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ኃይሏል ፡
በሥልጣን ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ተሹሟል
በሞገስ ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ደምቋል ፡
በዝና ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ታውቋል ፡
ኢየሱስ ፡ ከሁሉም ፡ ይልቃል ፭
ማደሪያው ፡ የተለየ ፡ ነው ፡ ከአማልክት ፡ ሁሉ
ለዘለዓለም ፡ የሚኖር ፡ በሙሉ ፡ ኃይሉ
ባለግርማና ፡ ሞገስ ፡ የክብር ፡ ጌታ
ምሥጋና ፡ ክብር ፡ አምልኮ ፡ ይብዛለት ፡ ዕልልታ
ባለግርማና ፡ ሞገስ ፡ የክብር ፡ ጌታ
ምሥጋና ፡ ክብር ፡ አምልኮ ፡ ይብዛለት ፡ ዕልልታ
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ በማደሪያው ፡ ላይ
በክብርና ፡ በግርማው
ሳይለዋወጥ ፡ ሳይነዋወጥ
እንዲሁ ፡ እንደጵና ፡ ያለው
ከነችሎቱ ፡ ከነብርታቱ ፡ የሚኖረው
ኧረ ፡ ይሄ ፡ ማነው
የአማልክት ፡ አምላክ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡
እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ነው
በክብር ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ከብሯል
በኃይል ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ኃይሏል ፡
በሥልጣን ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ተሹሟል
በሞገስ ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ደምቋል ፡
በዝና ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ታውቋል ፡
ኢየሱስ ፡ ከሁሉም ፡ ይልቃል ፭
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ በማደሪያው ፡ ላይ
በክብርና ፡ በግርማው
ሳይለዋወጥ ፡ ሳይነዋወጥ
እንዲሁ ፡ እንደጵና ፡ ያለው
ከነችሎቱ ፡ ከነብርታቱ ፡ የሚኖረው
ኧረ ፡ ይሄ ፡ ማነው
የአማልክት ፡ አምላክ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡
እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists