Kishore Kumar Hits

Azeb Hailu - እረኛዬ lyrics

Artist: Azeb Hailu

album: በመጀመርያ እግዚአብሔር


ስለበዛልኝ ምህረቱ ስለደገፈኝ ፀጋው
መቋጫ ከቶ አጣሁኝ ሳወራው ቢመሽ ቢነጋ
የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ የበጐ ነገር መገኛ
የሆነው ጌታ እግዚአብሔር እርሱ ነው የኔ እረኛ
ስለበዛልኝ ምህረቱ ስለደገፈኝ ፀጋው
መቋጫ ከቶ አጣሁኝ ስዘምር ቢመሽ ቢነጋ
የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ የበጐ ነገር መገኛ
የሆነው ጌታ ኢየሱስ እርሱ ነው የኔ እረኛ
እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ
እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ
እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪)
በምድር ላለው ህይወቴ ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ
መች ያልቃል የርሱ ቸርነት ተዘርዝሮና ተነግሮ
አምላኬ ለኔ ያረገው ባወራው ከቁጥር በዛ
ልዘምር እንጂ ሳልሰለች ሳልቆጥበው እንደ ዋዛ
እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ
እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ
እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪)
አጥኖ ፀሃይን ሞቆ የአንተን ምስጋና ካወራ
ምህረትህን ያየሁ እኔ እኔማ እንዴት አላወራ
በልጅህ የአንተ ልጅ ሆኜ ገብቼ ደጅህ ተከፍቶልኝ
ያየሁት እና የቀመስኩት የምለው ብዙ ነገር አለኝ
እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ
እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ
እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪)
ሙሉ ሆኖ እንደሚፈስ እንደ ውሀ ነው ሰላሜ
በክርስቶስ ባገኘሁት የህይወት ቃል ነው መለምለሜ
ከማይነጥፍ ከማይደርቀው የህይወት ምንጭ ተጠግቼ
የዚህን አለም በረሃ የድርቅ ወሬ መች ፈርቼ
እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ
እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ
እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists