Kishore Kumar Hits

Azeb Hailu - በርታ lyrics

Artist: Azeb Hailu

album: በመጀመርያ እግዚአብሔር


በሕይወት ፡ ጉዞ ፡ ላይ
ቢያደከም ፡ መንገዱ
የፈተናው ፡ ብዛት ፡ ዉጣ ፡ ውረዱ
ግን ፡ የያዝከው ፡ ተስፋ
ከአምላህ ፡ ከጌታ
የጰና ፡ ነውና ፡ ወገኔ ፡ በርታ
የጰና ፡ ነውና ፡ ወገኔ ፡ በርታ
ምናልባትም ፡ በጊዜያዊ ፡ ፈተና ፡ ተጨቀሃል
በብዙማ ፡ በብዙ ፡ ሃዘን ፡ በቅሶ ፡ ውስጥ ፡ አልፈሃል
ግን ፡ ያሁኑ ፡ የሚያበቃ ፡ የሚያከትም ፡ የሚያልፍ ፡ ነውና
ለዘላለም ፡ የፅና ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህና
አይዞህ ፡ በርታ ፡ ጭክን ፡ በል ፡ በእምነት ፡ ፅና
እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና
እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና
በምድር ፡ ላይ ፡ የሰው ፡ ሕይወት ፡ ሰልፍ ፡ ነው ፡ የጦር ፡ ሜዳ
ሕይወት ፡ ሩጫ ፡ ለማዘግየት ፡ የሚጥር ፡ የሚጐዳ
ጦርነቱን ፡ ለማሸነፍ ፡ ብትፈልግ ፡ ልትረታ
አስተውለው ፡ የሰጠህን ፡ ክቡር ፡ ቃል ፡ የአንተ ፡ ጌታ
አይዞህ ፡ በርታ ፡ ጭክን ፡ በል ፡ በእምነት ፡ ፅና
እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና
እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና
አለኝ ፡ ያልከው ፡ በጅህ ፡ ያለው ፡ ተበትኖ ፡ ቢጠፋ
ግራ ፡ ቀኙ ፡ ቢዘጋብህ ፡ ብታጣ ፡ የሚሆን ፡ ተስፋ
ሰማያትን ፡ ምድርን ፡ የሰራው ፡ ጌታ ፡ ረዳትህ
ብሰማው ፡ ብትፈቅድ ፡ ለአፍታ ፡ ጊዜ ፡ ሰተህ
አይዞህ ፡ በርታ ፡ ጭክን ፡ በል ፡ በእምነት ፡ ፅና
እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና
እመጣለሁ ፡ ያለህ ፡ ጌታ ፡ ይመጣልና
በሕይወት ፡ ጉዞ ፡ ላይ ፡
ቢያደከም ፡ መንገዱ ፡
የፈተናው ፡ ብዛት ፡ ዉጣ ፡ ውረዱ
ግን ፡ የያዝከው ፡ ተስፋ ፡
ከአምላህ ፡ ከጌታ
የፀና ፡ ነውና ፡ ወገኔ ፡ በርታ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists