Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Amanuel lyrics

Artist: Sofia Shibabaw

album: Fetenelegne, Vol. 3


ሊያድነን እንጂ ሊፈርድብን ወደ ዓለም ያልመጣው
መንገድ እውነት ሕይወት እሱ ብቻ ጌታ የሆነው
እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም ኢየሱስ ነው
ሞትን ድል ነስቶ በሲዖል ያሉትን ያወጣቸው
በትንሣኤው ኃይል ተለይተን ከሞት መንደር ወጣን
ከጌታ ጋራ በከበረው በአብ ቀኝ ተቀመጥን
አማኑኤል አማኑኤል አማኑኤል
እግዚአብሔር ወድዷል ሊሆን ከእኛ ጋር
አማኑኤል አማኑኤል አማኑኤል
እግዚአብሔር ወድዷል ሊሆን ከእኛ ጋር
የጎልጎታው ጀግና የጎልጎታው አርበኛ
ነፍሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ የሰጠ እረኛ
የጎልጎታው ጀግና የጎልጎታው አርበኛ
ነፍሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ የሰጠ እረኛ
አማኑኤል አማኑኤል አማኑኤል
እግዚአብሔር ወድዷል ሊሆን ከእኛ ጋር

የደህንነታችን ተግሳጽ በእሱ ላይ ነበረ
ስለ በደላችን ደቀቀ
በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ
ህመማችንንም ተሸከመ
የደህንነታችን ተግሳጽ በእሱ ላይ ነበረ
ስለ በደላችን ደቀቀ
በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ
ህመማችንንም ተሸከመ
በእሱ ቁስል እኛ ተፈወስን
ስለ እኛ ደህይቶ አበለጸገን
ይክበርልን ነጻ አውጥቶናል
ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል
ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል
ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል
ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል
ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል
የጎልጎታው ጀግና የጎልጎታው አርበኛ
ነፍሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ የሰጠ እረኛ
የጎልጎታው ጀግና የጎልጎታው አርበኛ
ነፍሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ የሰጠ እረኛ
አማኑኤል አማኑኤል አማኑኤል
እግዚአብሔር ወድዷል ሊሆን ከእኛ ጋር
ነጋሪት ይጎሰም ከበሮ ይመታ
ለነገሥታት ንጉሥ ለጌቶቹ ጌታ
ማደሪያው ይግባ እጥፍ ምስጋና
በእልልታ በጭብጨባ
አስር አውታር ባለው በገና

አማኑኤል ሊቀ ካህናችን
የፍቅር ሽልማታችን
ጓደኛ የሌለው እኩያ
የሀይማኖታችን ሐዋርያ
የጎልጎታው ጀግና የጎልጎታው አርበኛ
ነፍሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ የሰጠ እረኛ
የጎልጎታው ጀግና የጎልጎታው አርበኛ
ነፍሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ የሰጠ እረኛ
አማኑኤል አማኑኤል አማኑኤል
እግዚአብሔር ወድዷል ሊሆን ከእኛ ጋር

ሕይወቱን ለሰጠኝ ጌታ ሕይወቴን ሰጣለሁ
ወዶኛልና እኔም እወደዋለሁ
የናዝሬት ኢየሱስ አማኑኤል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል
ብቻውን ጌታ ነው ከፍ ይበል

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists