Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Egziabherin Amesginut lyrics

Artist: Sofia Shibabaw

album: Fetenelegne, Vol. 3


እግዚአብሔርን አመስግኑ
እግዚአብሔርን አመስግኑ
እግዚአብሔርን አመስግኑ
እግዚአብሔርን አመስግኑ
መካኒቱን ሳራ እንደ ቃሉ አሰባት
የእልፍ አዕላፋት እናት አደረጋት
ለባሪያው ለአብርሃም የተናገረውን
እንደ ምድር አሸዋ አበዛለት ዘሩን
ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ነውና
እግዚአብሔርን አመስግኑት
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ባሪያዎቹ አመስግኑት
ቅዱሳኑ አመስግኑት
መላእክቱ ያመስግኑት
ፍጥረት ሁሉ አመስግኑት
ዝቅ ዝቅ ያለውን ከመሬት አነሳ
ከአለቆች ጋራ ያስቀምጠው ዘንዳ
እንደ ምድር ትቢያ የተዋረደውን
ከፍ ከፍ አረገ አቀናው መንገዱን
ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ነውና
እግዚአብሔርን አመስግኑት
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ባሪያዎቹ አመስግኑት
ቅዱሳኑ አመስግኑት
መላእክቱ ያመስግኑት
ፍጥረት ሁሉ አመስግኑት
ምህረቱ ትዝ እያለው
ባሪያው እስራኤል ለዘላለም ረዳው
ቃልኪዳኑ ትውስ እያለው
ባሪያው እስራኤል ለዘላለም ረዳው
ይረዳናል ያግዘናል
ቃልኪዳኑን ዛሬ ያስታውሰዋል
ይረዳናል ያግዘናል
ምህረቱ ዛሬ ያስበናል
ለአዲስ ኪዳን ውበት ከአብ ውስጥ ለወጣው
ምስጋና ላሳርግ ለኔ ለታረደው
ቸርነቱ በዝቷል እንደማይቆም ጅረት
ከቤተ መቅደሱ ምስጋና ይብዛለት
ታውቀኝ ዘንድ እኔ ምንድነኝ
ትጎበኘኝ ዘንድ ኧረ እኔ ማነኝ
ታውቀኝ ዘንድ እኔ ምንድነኝ
ታስበኝ ዘንድ ኧረ እኔ ማነኝ
ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ነውና
ሰማይ ሰማያት አመስግኑት
በአርያም አመስግኑት
ከዋክብቱ አመስግኑት
ፀሀይ ጨረቃ አመስግኑት
ቅዱሳኑ አመስግኑት
በመሰንቆ አመስግኑት
በጽናጽል አመስግኑት
በከበሮ አመስግኑት
ሴቶች ወንዶች አመስግኑት
ሽማግሌዎች አመስግኑት
ህፃናቱ አመስግኑት
ፍጥረት ሁሉ አመስግኑት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists