Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Beesat Yat'mkal lyrics

Artist: Sofia Shibabaw

album: Sima Belew, Vol. 2


ሰው ማነህ ሳይባል እከሌ ነኝ ይላል
ከስሙ አስቀድሞ ያለ የሌለ ነገር ጨማምሮ ይናገራል
ስራህስ ምንድነው ብለው ቢጠይቁት
አሳምሮ ያወራል ያብራራል ከሰሙት
ለመጥመቁ ዮሐንስ ይኼ ዕድል ደረሰው
አንተ ማነህ ብሎ ብዙ ሕዝብ ጠየቀው
እንዲህ ሲል መለሰ ስለ ማንነቱ
ሳያፍር ገለጠ እውነቱን ከውሸቱ
እኔ ጠራጊ ነኝ ድምፅ ነኝ ምጮኸው
መንገድ የማዘጋጅ ከኋላ ሄዳለው
አይደለሁም ኤልያስ ከነብያቶች አንዱ
የማመቻች ነኝ ጥርጊያ ለመንገዱ
አላቸው መልሶ ራሱን አሳንሶ
የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ
ከእርሱ አንሳለሁኝ
እኔ ላንስ ይገባል እርሱ ከእኔ ይበልጣል
እኔ በውኃ ሳጠምቅ በእሳት ያጠምቃል
እርሱ ከእኔ ይበልጣል
እንዲህ ነው እንግዲህ ትህትና
እንዲህ ነው እንግዲህ ዝቅ ማለት
እንዲህ ነው እንግዲህ ትህትና
እንዲህ ነው እንግዲህ ዝቅ ማለት
ራስን ማወቅ ማንነትን
ሰው መሆንን መረዳትን
ያበዛዋል መዋረድን
ሒሳቡ ደግሞ ይሄ ነው
ዝቅ ያለ ነው ከፍ የሚለው
ሒሳቡ ደግሞ ይሄ ነው
ዝቅ ያለ ነው ከፍ የሚለው
እኔ እኔ እኔ እኔ እኔ እኔ ባልኩኝ ቁጥር
እወጣለሁኝ ካለሁበት አጥር
እኔ እኔ እኔ እኔ እኔ እኔ ያልኩኝ ለታ
ያበቃልኛል የማታ የማታ
እኔነቴ መድከሚያዬ
እኔነቴ መውደቂያዬ
እኔነቴ መሞቻዬ
እኔነቴ መቃብሬ
ስንቱ ተቀበረ በእኔነት መቃብር
ትንሳዔ ያምጣለት ትሁቱ እግዚአብሔር
ስንቱ ተቀበረ በእኔነት መቃብር
ትንሳዔ ያምጣለት ትሁቱ እግዚአብሔር
እንደ እንጀራ አይለመን ትህትና
መለወጥ ነው ፣ መወሰን ነው ፣ የሚያስፈልገው
በትዕቢት ለጋለው
እኔነቴ መድከሚያዬ
እኔነቴ መውደቂያዬ
እኔነቴ መሞቻዬ
እኔነቴ መቃብሬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists