Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Melkam Neh lyrics

Artist: Sofia Shibabaw

album: Sima Belew, Vol. 2


መልካም ነህ ለእኔ አባቴ
መልካም ነህ ለእኔ አባቴ
ታስብልኝ የለም ወይ አንተም ልጄን ብለህ
ሁልጊዜ ለእኔ መልካም ነህ
መልካም ነህ ለእኔ አባቴ
መልካም ነህ ለእኔ አባቴ
ታስብልኝ የለም ወይ አንተም ልጄን ብለህ
ሁልጊዜ ለእኔ መልካም ነህ

ይሁንልኝ ብዬ የተሟገትኳቸው
ባለፈው ዘመኔ ኧረ ብዙ ናቸው
ጊዜ ፈጀሁ እንጂ ከወዲህ ከወዲያ
ግን ጥልቅ አስብሎ ደርሶ በአንተ ሞያ
ትክክል ነህ ጌታ በሥራህ ጻድቅ ነህ
አንተ አትታረምም እንዲህ አድርግ ተብለህ
መልካም ነህ ለእኔ አባቴ
መልካም ነህ ለእኔ አባቴ
ታስብልኝ የለም ዎይ አንተም ልጄን ብለህ
ሁልጊዜ ለእኔ መልካም ነህ

እንደው መጨነቄ ሁሉ ከልኩ አያልፍ
አንዳችም ላልጨምር አንዳችም ላላተርፍ
ባይገቡኝም እንኳን መንገዶቼ ሁሉ
ለአንተ ግን አባቴ ጠርተው ይታያሉ
ከእኔ የምታስበው መልካም ከሆነልኝ
እንዳረከኝ ልሁን የእኔስ ይቅርብኝ
እኔ ያልኩት አልሆነም አንተ ያልከው አልቀረም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ ስኖር በዚች ዓለም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ ስኖር በዚች ዓለም
እኔ ያልኩት አልሆነም አንተ ያልከው አልቀረም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ ስኖር በዚች ዓለም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ ስኖር በዚች ዓለም

እግሮቼን ከወጥመድ ማነው ያወጣቸው
ዓይኖቼ ሁልጊዜ ጌታ ወደ አንተ ናቸው
በመረጥከው መንገድ አስተምረኸኛል
የማያልፈውን ሕይወት መኖር ይሻለኛል
የማያልፈውን ነብይ መስማት ይሻለኛል
መልካም ነህ ለእኔ አባቴ
መልካም ነህ ለእኔ አባቴ
ታስብልኝ የለም ዎይ አንተም ልጄን ብለህ
ሁልጊዜ ለእኔ መልካም ነህ
መልካም ነህ ለእኔ አባቴ
መልካም ነህ ለእኔ አባቴ
ታስብልኝ የለም ዎይ አንተም ልጄን ብለህ
ሁልጊዜ ለእኔ መልካም ነህ
እኔ ያልኩት አልሆነም አንተ ያልከው አልቀረም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ ስኖር በዚች ዓለም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ ስኖር በዚች ዓለም
እኔ ያልኩት አልሆነም አንተ ያልከው አልቀረም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ ስኖር በዚች ዓለም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ ስኖር በዚች ዓለም
ትክክል ነህ ጌታ በሥራህ ጻድቅ ነህ
አንተ አትታረምም እንዲህ አድርግ ተብለህ
ትክክል ነህ ጌታ በሥራህ ጻድቅ ነህ
አንተ አትታረምም እንዲህ አድርግ ተብለህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists