Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Yesus Melesegn lyrics

Artist: Sofia Shibabaw

album: Sima Belew, Vol. 2


ስለ ጻድቅ ሰው የሚሞት መቼም ቅርብ ይገኝ
እንዴት ተገኘ ብዬ አያስደንቀኝ
ስለ ቸር ሰው ቢሆን እንደዚሁ ነኝ እኔ
ጊዜዬን በዚህ አልፈጅም ለምኔ ለምኔ
አንድ ነገር አለ እኔን ያስደነቀኝ
ደካማ እያለሁ ሳላውቀዉ ያወቀኝ
ከሃጢያት ያራቀኝ ከመንገድ አውጥቶ
ኢየሱስ መለሰኝ ሞቴን ሁሉ ሞቶ አሃሃሃ
እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወድደው
እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወድደው
በአንዱ አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢያተኛ ሆኑ
ከዲያብሎስ ጋራ ገሃነም ሊጣሉ
በኢየሱስ መታዘዝ ከፍርድ አምልጠናል
የመንግሥተ ሠማይ ወራሽ አድርጐናል
እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወድደው
እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወድደው
ዝቅ ዝቅ ያለው ኢየሱስ ከሁሉ ይበልጣል
ለእኔ ባረገው ነገር ልቤ ተሸንፏል
የፍቅርንም ሚስጥር ያወኩት በእሱ ነው
አቀበት ዳገቱን የወጣው ለእኔ ነው
በደሙ ጸድቄ ከቁጣ ድኛለሁ
ጠላትነት ቀርቶ ወገን ተብያለሁ
ሰላሙን ሰብኮኛል የሰላም አለቃ
የጭንቀቱ ዘመን ከእኔ ላይ አበቃ አሃሃሃ
(እንዴት ያለ ፍቅር ነው)
እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወድደው
እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወድደው
እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወድደው
እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወድደው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists