Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Bekeraniwos Lay lyrics

Artist: Sofia Shibabaw

album: Sima Belew, Vol. 2


ሃፍረት አስቀርቅሮ አንገቴ ላይል ቀና
የበደሌ ቀንበር በላዬ በጸና
በቀራንዮ ላይ ባፈሰስከው ደምህ
ድፍረት ሆኖልኛል እንድቆም በፊትህ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ አምላኬ
ክብሬ ነህ ማዕረጌ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ አምላኬ
ክብሬ ነህ ማዕረጌ
ሥምህን ጠርቼ ድኛለሁኝና (አምላኬ)
በላይ በላዩ ላይ ልደርብ ምሥጋና (አምላኬ)
ኧረ እኔ አመለጥኩኝ አንተን በማመኔ (አምላኬ)
በሰውነቴ ላይ ታወቀኝ መዳኔ (አምላኬ)
ታዲያ እንዴት ዝም ይላል የተደረገለት (አምላኬ)
በድቅድቅ ጨለማ ብርሃን የሆንክለት (አምላኬ)
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ አምላኬ
ክብሬ ነህ ማዕረጌ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ አምላኬ
ክብሬ ነህ ማዕረጌ
አንተን በመምረጤ አላፈርኩም ከቶ
ሰላም ሆኖልኛል ቃልህ ልቤ ገብቶ
መታመኛዬ ነህ ኮርቼብሃለሁ
በሕይወቴ ዘመን አንተን አመልካለሁ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ አምላኬ
ክብሬ ነህ ማዕረጌ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ አምላኬ
ክብሬ ነህ ማዕረጌ
ስገጅ ስገጅ አለኝ ተገርፈሃልና (አምላኬ)
ልሰጥ የሚገባኝ ይኸው የእጅ መንሻ (አምላኬ)
ግሩም የዕርቅ ቀን ስለሆነ ለእኔ (አምላኬ)
ምሥጋናዬ ይኸው ይፈሳል ከልቤ (አምላኬ)
ከጻድቃን ማህበር እኔም ልቀላቀል (አምላኬ)
ለዚህ በቅቻለሁ ለክብር ልታሰብ (አምላኬ)
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ አምላኬ
ክብሬ ነህ ማዕረጌ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ አምላኬ
ክብሬ ነህ ማዕረጌ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ አምላኬ
ክብሬ ነህ ማዕረጌ
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ አምላኬ
ክብሬ ነህ ማዕረጌ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists