Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Aloyie lyrics

Artist: Sofia Shibabaw

album: Sima Belew, Vol. 2


ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ
ላማ ፡ ሰበቅታኒ

ይገባ ፡ ነበር ፡ ወይ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ማልቀስህ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ወይ ፡ እንዲያ ፡ መዋተትህ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ወይ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ መሞትህ
ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ

ይዘዉህ ፡ ሲሄዱ ፡ እንደሚታረድ ፡ በግ
ዝም ፡ ብለህ ፡ እየሄድክ ፡ አንዳች ፡ ሳትሟገት
ማነኝ ፡ ለመሆኑ ፡ እንዴት ፡ የተወደድኩኝ?
ከክብር ፡ ላይ ፡ ወርደህ ፡ የተዋረድክልኝ
አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ
አቤቱ ፡ መውደድህ ፡ ስፋቱ
አይመረመርም ፡ በሰው ፡ ዘንድ
ታላቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መውደድ

ፊቴ ፡ ድቅን ፡ ይላል ፡ የእሾህ ፡ ጉንጉኑ
የጅራፉ ፡ ብዛት ፡ የገላ ፡ ሰንበሩ
ኤሎሄ ፡ ኤሎሄ ፡ ላማ ፡ ሰበቅታኒ
ብለህ ፡ ስትጨነቅ ፡ ስለእኔ ፡ ስትማቅቅ
አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ
አቤቱ ፡ መውደድህ ፡ ስፋቱ
አይመረመርም ፡ በሰው ፡ ዘንድ
ታላቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መውደድ

ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ ጻድቅ ፡ አይደለህ ፡ ዎይ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ ንጹህ ፡ አይደለህ ፡ ዎይ
ጻድቅ ፡ ሰው ፡ በመስቀል ፡ እርቃኑን ፡ አደረ
ስለ ፡ ኃጢያተኞች ፡ ደሙን ፡ አፈሰሰ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ማልቀስህ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ እንዲያ ፡ መዋተትህ
ይገባ ፡ ነበር ፡ ዎይ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ መሞትህ
ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ ወይ
አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ
አቤቱ ፡ መውደድህ ፡ ስፋቱ
አይመረመርም ፡ በሰው ፡ ዘንድ
ታላቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ መውደድ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists