Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Wha End Lielew lyrics

Artist: Sofia Shibabaw

album: Sima Belew, Vol. 2


የኔ ምስጋና
ዝናብ እንደሌለው ደመና
ውሃ እንደሌለው ደመና
አይደለም የኔ ምስጋና
የኔ ምስጋና
ዝናብ እንደሌለው ደመና
ውሃ እንደሌለው ደመና
አይደለም የኔ ምስጋና
ወይ ዘንቦ ላይዘንብ ወይ ጥሎ ላይጥል
መብረቁ ሲያስፈራ ሲል ብልጭ ድርግም ድርግም
ነጎድጓዱ ተምሞ ጠብ እንኳን ካላለ
ዝናብ ፈርቶ ሰዉ እቤቱ ከዋለ ተታለለ
ግርግርም ባይኖር ሙዚቃም ባልሰማ
የነፍሴ ምስጋና ዙፋኑ ይሰማ
ዝናብ እንደሌለው ደመና
አይደለም የኔ ምስጋና
የኔ ምስጋና
ዝናብ እንደሌለው ደመና
ውሃ እንደሌለው ደመና
አይደለም የኔ ምስጋና
እህሉ ሊበላሽ ዘንቦበት በረዶ
እያለ ሲያወራ ካሁን አሁን ወርዶ በረዶ
ጉሙ ሲያጉረመርም መጣሁኝ እያለ
ደመናው ሰንጥቆት ፀሐይ ብቅ ካለ ተታለለ
ዝም ብዬ የምጮህ እንዲያው ባዶ ሜዳ
አይደለሁም እኔስ ሞልቶኛል ምስጋና
ዝናብ እንደሌለው ደመና
አይደለም የእኔ ምስጋና
ምስጋና ምስጋና ምስጋና ምስጋና
እሰዋለሁ ለጌታዬ ለአምላኬ
ይገባዋልና በከፍታ በዝቅታ
አምልኮዬን አቀርባለሁ ለእርሱ ክብር በደስታ
ምስጋና ምስጋና ምስጋና ምስጋና
ለጌታዬ ለታደገኝ ለአዳነኝ
ለክብሩ ዝቅ እያልኩኝ እየሰገድኩ እያመለኩ
ፊቱ ብወድቅ ባደንቀው ባሞግሰው ለእርሱ አይበቃም
የኔ ምስጋና
ዝናብ እንደሌለው ደመና
ውሃ እንደሌለው ደመና
አይደለም የኔ ምስጋና
የኔ ምስጋና
ዝናብ እንደሌለው ደመና
ውሃ እንደሌለው ደመና
አይደለም የኔ ምስጋና

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists