Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Leka Alie Dagna lyrics

Artist: Sofia Shibabaw

album: Fikir Kemekabir Belay, Vol.1


አዝ፦ ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ (፪x)
የማይቀበል ጉቦ መማጸኛ
ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ
በቅን የሚፈርድ የማይወናበድ
ግራና ቀኙን አይቶ ማይዘላብድ
ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ (፪x)
ነፃ አወጣኝ ሆኖ ጠበቃ
ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ
ከሳሼ ተነስቶ ስራውን መስርቶ
የጠቀመኝ መስሎ ጐትጉቶ ጐትጉቶ
ስራውም ተሳክቶ እኔንም አስቶ
መልሶ ከሰሰኝ እንዲፈረድብኝ
ከዳኛው አቆመኝ ጠበቃ ሳይኖረኝ
የችሎቱም ዳኛ አባቴ ሆነና
ተከስሼ ስቀርብ በልቡ አዘነና
ሞታ አትቀርም እሷ ብሎ አሰበና
ሞቷን እሞታለሁ ብሎ በየነልኝ
በኔው ሐጥያት እርሱ ጌታዬ ሞተልኝ
ሞተልኝ ሞተልኝ ሞተልኝ ጌታዬ ታደገኝ
ሞተልኝ ሞተልኝ ሞተልኝ ኢየሱሴ ታደገኝ
አዝ፦ ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ (፪x)
የማይቀበል ጉቦ መማጸኛ
ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ
በቅን የሚፈርድ የማይወናበድ
ግራና ቀኙን አይቶ የማይዘላብድ
አዝ፦ ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ (፪x)
ነፃ አወጣኝ ሆኖ ጠበቃ
ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ
ነፍሴን እንደ ጭልፊት ሲነዳት ከፊት ፊት
ወስዶ ቢከሳትም ትልቁ ዳኛ ፊት
ከነአደፈው ልብሴ ተጐናጽፋ ነፍሴ
ገልጦ ገበናዬን አሳይቶ ጉዴን
ሊያሳጣኝ ከችሎት ያዋረደኝ መስሎት
እድፋሙ ጥምጣም ቢታሰርም በጣም
አዘዘ ግን ዳኛው ፍርድ እስከ ወዲያኛው
ይፈታ ጥምጣሙ ኮተታ ኮተቱ
እንኪ አዲሱ ልብስሽ ታዪ ተጐናጽፈሽ
ወጥተሻል አርነት ሂጂ በነፃነት
አርነት አርነት አርነት ሄድኩኝ በነፃነት
አርነት አርነት አርነት ወጣሁ በነፃነት
አዝ፦ ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ (፪x)
የማይቀበል ጉቦ መማጸኛ
ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ
በቅን የሚፈርድ የማይወናበድ
ግራና ቀኙን አይቶ የማይዘላብድ
ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ (፪x)
ነፃ አወጣኝ ሆኖ ጠበቃ
ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ
ለካ አለ ዳኛ እውነተኛ ለካ አለ ዳኛ (፬x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists