Kishore Kumar Hits

Sofia Shibabaw - Fikir Kemekbir Belayi lyrics

Artist: Sofia Shibabaw

album: Fikir Kemekabir Belay, Vol.1


ፍቅር እስከ መቃብር
ፍቅር እስከ መቃብር
ፍቅር እስከ መቃብር
ፍቅር እስከ መቃብር
የስንቶች ፍቅር እስከ መቃብር
የኛ ግን ኢየሱስ የኛ ግን ኤልሻዳይ
የርሱ ፍቅር ያልፋል ከመቃብር በላይ
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር
ፍቅርን የተራበ ፍቅርን የተጠማ ከውስጡ ከአንጀቱ
ስለፍቅር አይነት ቢሰማ አይሰለቸው ተርቧል ከእውነቱ
አውቋል አንድ ነገር የፍቅርን መቋጫ የመጨረሻውን
ከመቃብር ድረስ የገባውን ኪዳን ውሉን ማስረጃውን
ግን ደግሞ አለ ሌላ መቃብር ያለፈ ፍቅሩ ያልተሸነፈ
በፍቅር ተይዞ ያለምክንያት ወርዶ ከመቃብር ማዶ
ተቀብሮ ያልቀረ ጥሶ የተሻገረ ጭራሹን ያረገ
ሞቶ የተነሳ ሃዘን የሚያስረሳ የይሁዳ አንበሳ
በምድር ያለ ሁሉ ቢጠራ ቢጠራ ለችግረኛ ሰው ምኑ ነው የሚራራ
ሞትህ ለኔ ይሁን እያለ ሰው ውሸቱን በስራ ያሳየ አግኝተናል አንዱን
ከመቃብር በላይ ፍቅሩን የገለጠ ቢጠቀስ አንድ የለም ከጌታ የበለጠ
ከጌታ የበለጠ
ከጌታ የበለጠ
ፍቅር እስከ መቃብር
ፍቅር እስከ መቃብር
ፍቅር እስከ መቃብር
ፍቅር እስከ መቃብር
የስንቶች ፍቅር እስከ መቃብር
የኛ ግን ኢየሱስ የኛ ግን ኤልሻዳይ
የርሱ ፍቅር ያልፋል ከመቃብር በላይ
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር
በቁሙ የተጠላ የተኮራረፈ የሚዘጋበት በር
የሞቱ ቀን ደግሞ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል አብሮ ለመቀበር
መውደዱን ሲገልጽ በእንጉርጉሮ ዜማ አልቃሽ አስጠርቶ
የአርባው ዕለት ደግሞ ሙሾ ሲያወጣለት ሐውልት አሰርቶ
አቤት ሲዋደዱ ይላል ደግሞ ሌላው ነገሩ ያልገባው
ይደነቃል ብሎ የነዚህስ ፍቅር ነው እስከ መቃብር
አልሰማ የኔን ነገር ወዶኝ ስለሞተ ነፍሱን ስለሰጠ
የኔ ብርቱ አፍቃሪ ከመቃብር በላይ ሄዷል ወደሰማይ
በፍቅር እስራት ገመድ የገመደ ከሰው ጋር ሊወዳጅ ከላይ የወረደ
አብሮ ሄዶ ሄዶ ጫፍ እየደረሰ አይሰናበትም እየተመለሰ
ምድርና ሞላዋን ቢገለባብጠው ይምጣና ይወራረድ ጌታዬን አይበልጠው
ጌታዬን አይበልጠው
ጌታዬን አይበልጠው
ፍቅር እስከ መቃብር
ፍቅር እስከ መቃብር
ፍቅር እስከ መቃብር
ፍቅር እስከ መቃብር
የስንቶች ፍቅር እስከ መቃብር
የኛ ግን ኢየሱስ የኛ ግን ኤልሻዳይ
የርሱ ፍቅር ያልፋል ከመቃብር በላይ
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር
ፍቅር ያልፋል ከመቃብር

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists