Kishore Kumar Hits

Teddy Tadesse - Wa lyrics

Artist: Teddy Tadesse

album: Wa!, Vol. 3


በንጉስ ፈረስ ላይ ተቀምጦ
እድፋሙ ልብሱ ተለውጦ
በንጉስ ፈረስ ላይ ተቀምጦ
የመሞቴን ዜና ሊሰማ እንደቋመጠ ልክ እንደ ሐማ
እግዚአብሔር ሲፈርድልኝ ለኔ እንደ መርዶክዮስ ሆነ ዘመኔ
ምህረቱ ነው የከለለኝ
ቸርነቱ ነው የደገፈኝ
አጥፊዎች እያሉ በህይወት መኖሬ
ጥበቃው በዝቶ እንጂ እኔስ እስከ ዛሬ
ምህረቱ ነው የከለለኝ
ቸርነቱ ነው የደገፈኝ
ነገር ተገልብጦ የከሳሼ ወሬ
ውርደቴ ሲጠበቅ ተሰማ መክበሬ
ምህረቱ ነው የከለለኝ
ቸርነቱ ነው የደገፈኝ
አምላኩን ተማምኖ ደጁ ላይ ሆኖ ለታገሰው ሰው
እንዲህ ይደረጋል ንጉስ ለወደደው ደግሞም ላከበረው
የጠላትን ምክር ከንቱ አርጎልኝ የሰራውን ሴራ
ለክፉ ያሰበው ለመልካም ሆነልኝ ደርሶ የኔ ተራ
በንጉስ ፈረስ ላይ ተቀምጦ
እድፋሙ ልብሱ ተለውጦ
መለከት ይነፋ ይታወጅ አዋጅ
መስቀል ላይ ሟች ነበርኩ ቀይሮልኝ እንጂ
በፊቱ መውደቅ የጀመርክለት
አይሁድ ከሆነ ኪዳን ያለበት
ትነካውና ዋ!
የተባለልኝ ለኔ ነዋ
ትነካውና ዋ!
የተባለልኝ ለኔ ነዋ
ለኔ ነዋ
ለኔ ነዋ
ለኔ ነዋ
ስታመነው አየኝ
ስደገፈው አየኝ
ፍርዱ ለተዛባ እኔ አለሁለት አለኝ
ስታመነው አየኝ
ስደገፈው አየኝ
ፍርዱ ለተዛባ እኔ አለሁለት አለኝ
የመሞቴን ዜና ሊሰማ እንደቋመጠ ልክ እንደ ሐማ
እግዚአብሔር ሲፈርድልኝ ለኔ እንደ መርዶክዮስ ሆነ ዘመኔ
ምህረቱ ነው የከለለኝ
ቸርነቱ ነው የደገፈኝ
አጥፊዎች እያሉ በህይወት መኖሬ
ጥበቃው በዝቶ እንጂ እኔስ እስከ ዛሬ
ምህረቱ ነው የከለለኝ
ቸርነቱ ነው የደገፈኝ
ነገር ተገልብጦ የከሳሼ ወሬ
ውርደቴ ሲጠበቅ ተሰማ መክበሬ
ምህረቱ ነው የከለለኝ
ቸርነቱ ነው የደገፈኝ
አዋጅ ሲፈራረቅ ያለመናወጥ ጸንቶ የጠበቀ
ብድራቱን አይቶ ያላመቻመቸ ስፍራ ያለቀቀ
የኋላ የኋላ ውርደቱን በክብር ሀዘኑን በደስታ
ለውጦ ክሶታል ሊከፍለው ሲመጣ ያከበረው ጌታ
በንጉስ ፈረስ ላይ ተቀምጦ
እድፋሙ ልብሱ ተለውጦ
መለከት ይነፋ ይታወጅ አዋጅ
መስቀል ላይ ሟች ነበርኩ ቀይሮልኝ እንጂ
በፊቱ መውደቅ የጀመርክለት
አይሁድ ከሆነ ኪዳን ያለበት
ትነካውና ዋ!
የተባለልኝ ለኔ ነዋ
ትነካውና ዋ!
የተባለልኝ ለኔ ነዋ
ለኔ ነዋ
ለኔ ነዋ
ለኔ ነዋ
ስታመነው አየኝ
ስደገፈው አየኝ
ፍርዱ ለተዛባ እኔ አለሁለት አለኝ
ስታመነው አየኝ
ስደገፈው አየኝ
ፍርዱ ለተዛባ እኔ አለሁለት አለኝ
እኔ አለሁለት አለኝ
እኔ አለሁለት አለኝ
እኔ አለሁለት አለኝ
እኔ አለሁለት አለኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists