Kishore Kumar Hits

Teddy Tadesse - Elileta lyrics

Artist: Teddy Tadesse

album: Ayameregnim, Vol.1


ምን እላለሁ እኔ ምን እላለሁኝ
ምን እላለሁኝ
ምን እላለሁኝ
ስትረዳኝ እያየሁ ስታግዘኝ
ስታግዘኝ
ስታግዘኝ
የቱን ዘምሬ የቱን እተዋለሁ
ለኔ ያደረክልኝ ከአይምሮ በላይ ነው
ለኔ ያደረክልኝ ከአይምሮ በላይ ነው
መልካም ነህ ቢሉህ መልካምነትስ መቼ ይገልጽሃል
ፍቅር ነህ ቢሉህ የፍቅር ልኩ መቼ ይገልጽሃል
ኧረ ማን ልበልህ
ማን ልበልህ
ቃል አጣሁልህ
ኧረ ማን ልበልህ
ማን ልበልህ
ቃል አጣሁልህ
ከተጣልኩበት አዘቅት መተህ
ከጠላቴ እጅ እኔን ተናጥቀህ
በደምህ ገዝተህ ያንተ ካረከኝ
እንዴት አልዘምር እንዴት አልቀኝ
ዛሬማ በላይ ሆኗል ስፍራዬ
በአብ ቀኝ ሆኗል መቀመጫዬ
ክብር ምስጋና ላንተ ይድረስህ
እድሜ ዘመኔን ልዘምርልህ
እንዴት ላመስግንህ
ኧረ እንዴት ላወድስህ
ከቃላት በላይ ነፍሴን አፍስሼ
ሁለንተናዬን ላንተ ሰጥቼ
በፍቅርህ ጉልበት ተረትቻለሁ
ይኸው ላመልክህ መጥቻለሁ
ከቃላት በላይ ነፍሴን አፍስሼ
ሁለንተናዬን ላንተ ሰጥቼ
በፍቅርህ ጉልበት ተረትቻለሁ
ይኸው ላመልክህ መጥቻለሁ
መልካም ነህ ቢሉህ መልካምነትስ መቼ ይገልጽሃል
ፍቅር ነህ ቢሉህ የፍቅር ልኩ መቼ ይገልጽሃል
ኧረ ማን ልበልህ
ማን ልበልህ
ቃል አጣሁልህ
ኧረ ማን ልበልህ
ማን ልበልህ
ቃል አጣሁልህ
ሙት የነበርኩኝ በበደል ብዛት
ህያው አረከኝ ነፍሴን ቀደስካት
ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠኸኝ
በትልቅ ፍቅርህ እንዲያው ወደድከኝ
ጽድቄ ነህና ቅድስናዬ
እንከን የሌለህ ንጽህናዬ
ብቃት የለኝም የምለው የኔ
ቤዛ ባትሆነኝ አንተ መድህኔ
እንዴት ላመስግንህ
ኧረ እንዴት ላወድስህ
ከቃላት በላይ ነፍሴን አፍስሼ
ሁለንተናዬን ላንተ ሰጥቼ
በፍቅርህ ጉልበት ተረትቻለሁ
ይኸው ላመልክህ መጥቻለሁ
ከቃላት በላይ ነፍሴን አፍስሼ
ሁለንተናዬን ላንተ ሰጥቼ
በፍቅርህ ጉልበት ተረትቻለሁ
ይኸው ላመልክህ መጥቻለሁ
አመልክሃለው ዘላለሜ ኢየሱስ ያንተ ነው
አመልክሃለው የኔ ጌታ ዘመኔን ውረሰው
አመልክሃለው ዘላለሜ ኢየሱስ ያንተ ነው
አመልክሃለው የኔ ጌታ ዘመኔን ውረሰው
ዘመኔ ያንተ ነው(×2)
ኑሮዬ ያንተ ነው(×2)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists