Kishore Kumar Hits

Yidnekachew Teka - Bale Eda Ne lyrics

Artist: Yidnekachew Teka

album: Chekolebegne , Vol.1


የደህንነቴ መደምደሚያ
የክብር ስሜ ነህ መጠሪያ
ማዕረጌ ሆነህ በሞትህ
እኔም ተባልኩኝ ልጅህ
የደህንነቴ መደምደሚያ
የክብር ስሜ ነህ መጠሪያ
ማዕረጌ ሆነህ በሞትህ
እኔም ተባልኩኝ ልጅህ
የሞትህ ፍሬ የድካምህ
በጣር የወለድከኝ ልጅህ
በመከራ አልፈህ ያገኘኸኝ
የእንባ ልጅህ ነኝ
የሞትህ ፍሬ የድካምህ
በጣር የወለድከኝ ልጅህ
በመከራ አልፈህ ያገኘኸኝ
የእንባ ልጅህ ነኝ
°°°
እኔ ባለዕዳ ነኝ
እኔ የፍቅር ባለዕዳ ውለታ ያለብኝ
እንዴት እንዴት ብዬ ነው መክፈል የምችለው የፍቅርህን ሸክም
መቼም የማልመልሰው ልክፈል እንኳ ብዬ ብጀምር ማለዳ
ፍቅርህን እንዲያው ሰጠኸኝ ታዲያ አይደለሁም ወይ የፍቅርህ ባለዕዳ
መራመድ አይችሉም እግሮቼ
ኢየሱስ በፍቅርህ ተይዤ
እንዳልሄድ ከቶ ወደ ሌላ
አርገኸኝ የፍቅርህ እስረኛ
አርገኸኝ የፍቅርህ እስረኛ
እንዳልሄድ ከቶ ወደ ሌላ
ኢየሱስ በፍቅርህ ተይዤ
መራመድ አይችሉም እግሮቼ
ንግሥና መጣ በደምህ እኔ ባለዕዳ ነኝ
ክህነት መጣ በሞትህ ኧረ እኔ ባለዕዳ ነኝ
ደህንነት ሆነ በፀጋ እኔ ባለዕዳ ነኝ
ልጅ መባል ቢሆን በስራ ኧረ እኔ ባለዕዳ ነኝ
°°°
እኔማ የፍቅርህ ባለዕዳ የምህረትህ ባለዕዳ ነኝ መራመድ አይችልም እግሬ ተይዣለሁ እኔ
ነፍሱን ለወዳጁ ሚሰዋ
ይገኝ ይሆናል በመከራ
ኢየሱስ የአንተ ግን ሚገርመው
ለጠላትህ የሞትከው
ነፍሱን ለወዳጁ ሚሰዋ
ይገኝ ይሆናል በመከራ
ኢየሱስ የአንተ ግን ሚገርመው
ለጠላትህ የሞትከው
እድሜ ዘመኔን የሚገዛ
ልቤን የያዘ ውለታ
የፍቅር ዕዳ አኖርክብኝ
ሳልወድህ ወደኸኝ
እድሜ ዘመኔን የሚገዛ
ልቤን የያዘ ውለታ
የፍቅር ዕዳ አኖርክብኝ
ሳልወድህ ወደኸኝ
መልክና ውበትህ ጠፋ እኔ ባለዕዳ ነኝ
በሰው ተንቀህ ተጠላህ ኧረ እኔ ባለዕዳ ነኝ
ተፈወስኩኝ አንተ ቆስለህ እኔ ባለዕዳ ነኝ
ደዌ ህመሜን ወሰድህ ኧረ እኔ ባለዕዳ ነኝ
°°°

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists