Kishore Kumar Hits

Yidnekachew Teka - Kiber Yihun Lesimu lyrics

Artist: Yidnekachew Teka

album: Chekolebegne , Vol.1


በፈረስ ውድድር ወደ ትልቁ ሜዳ
ሁሉም ተሰማርቶ በድንገት ድል ቢነሳ
ተብሎ ቢጠየቅ ማነው ያሸነፈው
ፈረሱና ጌታው አንድ ላይ ተቀምጠው
እኔ ነኝ ሚለውን እስኪ ይጠየቅ ማነው
ጌታው አይደለም ዎይ ፈረሱን እያየሁ
እንዲህ ሲል ሰማሁት እንዲህ ሲል አምላኬ
ድል አድርጌያለሁኝ እኔማ በራሴ
ስለዚህ ስንኖር በዚህች ምድር ላይ
አምላክ እንዳለው ሰው እንደ ተወካይ
ስለእኛ ለሞተው ደግሞ ለተነሳው
የእርሱን ክብር እንጂ የእኛን ስራ እንርሳው
ክብር ይሁን ለዝናው (ክብር)
ክብር ይሁን ለስሙ (ክብር)
ክብር ይሁን ዘለዓለም (ክብር)
ክብር ይሁን ለተገባው
በሩጫም ውድድር ወደ ሩጫው ሜዳ
ሁሉም ተሰማርቶ በድንገት ድል ቢሰማ
ቶሎ የሚይዙት ሮጠው ይሄዱና
ባንዲራውን አይደል ሚለብሱት በተርታ
የወከላቸውን አገር መቼ ረሱ
ለስማቸው ብቻ አይሮጡም እነሱ
እንዲህ ሲል ሰማሁት እንዲህ ሲል አምላኬ
ድል አድርጌያለሁኝ እኔማ በራሴ
ስለዚህ ስንኖር በዚህች ምድር ላይ
አምላክ እንዳለው ሰው እንደ ተወካይ
ስለእኛ ለሞተው ደግሞ ለተነሳው
የእሱን ክብር አንጂ የእኛን ስራ እንርሳው
ክብር ይሁን ለዝናው (ክብር)
ክብር ይሁን ለስሙ (ክብር)
ክብር ይሁን ዘለዓለም (ክብር)
ክብር ይሁን ለተገባው
የኔ ጌታ መሆን ያማረኝ
የኔ ኢየሱሴን ስኖር በምድር
የኔ ጌታ በእኔ አልፈህ ሁንብኝ
የኔ ኢየሱስ ኢየሱስ (፪x)
ኢየሱስ ተቀምጦባት በዛች ውርንጭላ
ወደ ኢየሩሳሌም በክብር ሲገባ
ሆሳዕና ሲባል ሲዘመር ለክብሩ
ዘምባባው ሲነጠፍ ሁሉም ሆሆ እያሉ
ምትረግጠውን እንኳን ውርንጭላይቱ
ያነጠፉላትን ሳይገባ ንጉሡ
ለእርሷ አይደል ቀርቶ ይህ ሁሉ ሙገሳ
በፊት ማን አይቷታል ባለችበት ታስራ
እኛንም ኢየሱስ ከፈታን ለክብሩ
ልቡ ከወደደ ሊሰራብን እሱ
ጌታ መርጦን እንጂ ተክቶልኛል
የማንጠቅም ባሪያዎች አይደለንም እኛ
ክብር ይሁን ለዝናው (ክብር)
ክብር ይሁን ለስሙ (ክብር)
ክብር ይሁን ዘለዓለም (ክብር)
ክብር ይሁን ለተገባው
ሁለት ባሮች ታግለው በጥንቱ ጨዋታ
አንደኛው ሲሸነፍ አንዱ ድል ሲነሳ
ህዝቡ ይነሳና ለአሸናፊው ጌታ
ይጨፍርለታል ባሪያው እየሰማ
ምንም ቢያሸንፍ ባሪያው በጉልበቱ
ጌታው ዋጋ ከፍሎ አድርጐታል የራሱ
እንዲህ ሲል ሰማሁት እንዲህ ሲል አምላኬ
ድል አድርጌያለሁኝ እኔማ በራሴ
ስለዚህ ስንኖር በዚህች ምድር ላይ
አምላክ እንዳለው ሰው እንደ ተወካይ
ስለእኛ ለሞተው ደግሞ ለተነሳው
የእሱን ክብር አንጂ የእኛን ስራ እንርሳው
ክብር ይሁን ለዝናው (ክብር)
ክብር ይሁን ለስሙ (ክብር)
ክብር ይሁን ዘለዓለም (ክብር)
ክብር ይሁን ለተገባው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists