Kishore Kumar Hits

Yidnekachew Teka - Madanu Kefe Yale Newe lyrics

Artist: Yidnekachew Teka

album: Chekolebegne , Vol.1


ይወርሰኛል ብዬ የፈራሁት ነገር የቆመ በበር
አይሆንም አለ ጌታ ከሰማያት ቃል ወጣ ስለእኔ
ራራልኝ ውዴ
አይሆንም አለ ጌታ ከሰማያት ቃል ወጣ ስለእኔ
ራራልኝ ውዴ
ወጀብ አለ ከፊት አትፍራ አለኝ ጌታዬ
ተገልብጧል ነገሩ ቃል ወጥቷል ዛሬ ለእኔ
በመንገድ ሊያስቀረኝ ሊገታኝ የነበረ
ቀደምኩት አለኝ ጌታ ወጥመዱ ተሰበረ
ማነው ማዕበሉን የገሰጸው
ማነው ወጀቡን ጸጥ ያደረገው
ማነው ይሁን ሲል ሚሆንለት
ማነው የአፉ ቃል ሚጸናለት
ጌታዬን ነው ጌታዬ ያየሁት በዘመኔ
ጌታዬን ነው ጌታዬ ያየሁት በዘመኔ
ፈርቶት ከሩቅ ዘመኔን ቢነሳ ያ ጠላቴ
ጉልበቴን ሊያደክመው ቢቆምም በመንገዴ
ይሄዳል የኔ ነገር በቃል ሚኖር አይቆምም
ሰባሪው ከፊት ወጥቷል ሰብሬ አልፋለሁ እኔ
ማነው መንገዴን ያስጀመረኝ
ማነው መንገዴን ሚያስጨርሰኝ
ማነው ከፊቴ የቀደመው
ማነው መንገዴን የከፈተው
ጌታዬን ነው ጌታዬ ያየሁት በዘመኔ
ጌታዬን ነው ጌታዬ ያየሁት በዘመኔ
ንጉሥ ወርዶ ከሰማይ አይቆምም ፊቱ ከልካይ
ይታደጋል ያድናል ደርሶ ከሞት ያወጣል
እኔም የእርሱ ልጅ ሆኜ ድኛለሁ ከጠላቴ
ጠላት ያሴረው ሴራ መና ሆነ ፉከራ
ማዳኑ ከፍ ያለ ነው
ኢየሱስ ከፍ ያለ ነው
ሲረዳኝ ከፍ ያለ ነው
ሲያወጣኝ ከፍ ያለ ነው
ጌታ ሲረዳኝ
ጌታ ሲያወጣኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists