Kishore Kumar Hits

Samuel Negussie - Anten Bemamene lyrics

Artist: Samuel Negussie

album: Be'egziaber Alem, Vol. 1


የከፍታ ፡ ዘመን ፡ የብርሃን ፡ ሕይወት
የሚጨምር ፡ ሰላም ፡ የሚጨምር ፡ ደስታ
የክብር ፡ ዘመን ፡ ነው ፡ ከፊቴ ፡ ያለው
መልካሙን ፡ አዋጅ ፡ እኔ ፡ አውጃለው
ጨለማው ፡ አልፎ ፡ ያለቀስኩበት
ዛሬ ፡ ብርሃን ፡ ሆንዋል ፡ ኧረ ፡ በእኔስ ፡ ሕይወት
አለም ፡ ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ይህን ፡ ይወቅልኝ
ምክንያቱም ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ስላለኝ
ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ በማመኔ (፫x)
ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ በማመኔ (፫x)
ባርነቴ ፡ ቀርቶ ፡ ወራሽ ፡ ሆንኩ ፡ እኔ
ወራሽ ፡ ሆኛለው ፡ ወራሽ ፡ ሆኛለው (፪x)
ወራሽ ፡ ሆኛለው ፡ ወራሽ ፡ ሆኛለው ፡ አሄ
ወራሽ ፡ ሆኛለሁ ፡ ልጅህ ፡ ሆኛለሁ
ይኸው ፡ በደስታ ፡ አንተን ፡ አመልካለው

ስላምና ፡ ደስታ ፡ ዕረፍት ፡ ሆነ ፡ ቤቴ
መዳኔ ፡ ዕውን ፡ ሆነ ፡ ሳስገባው ፡ ወደ ፡ ቤቴ
ነፃነቴን ፡ ላውጅ ፡ ከግዞት ፡ መውጣቴን
በብርሃን ፡ አለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆኔን
ከእንግዲ ፡ ጨለማ ፡ በእኔ ፡ ሕይወት ፡ የለም
ሞት ፡ መውጊይው ፡ ተሰብርዋል ፡ እኔን ፡ አይነካኝም
እርግማኔን ፡ ሽረህ ፡ ፅድቅን ፡ አለበስከኝ
በማመኔ ፡ ብቻ ፡ ወራሽ ፡ አደረከኝ
ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ በማመኔ (፫x)
ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ በማመኔ (፫x)
ባርነቴ ፡ ቀርቶ ፡ ወራሽ ፡ ሆንኩ ፡ እኔ
ይሁንልህ ፡ ምሥጋና ፡ ይሁንልህ ፡ ዝማሬ
ይሁንልህ ፡ አምልኮ ፡ ይሁንልህ ፡ ጌታዬ (፪x)
ከሞት ፡ ድኛለሁና ፡ ከሞት ፡ ድኛለሁና ፡ ከሞት
ከሞት ፡ ድኛለሁና ፡ ላንተ ፡ ምስጋና

የደም ፡ ነው ፡ ኪዳኑ ፡ የተሳሰርንበት
ከፍሎልኛል ፡ ዋጋ ፡ ያንድ ፡ ልጁን ፡ ህይወት
ሆኖኛል ፡ አባቴ ፡ እኔም ፡ ደግሞ ፡ ልጁ
ወራሽ ፡ አድርጎኛል ፡ የሰማይ ፡ የምድሩ
የክብር ፡ የከፍታ ፡ የደስታ ፡ መሆኑን
አረጋግጫለው ፡ የቀረው ፡ ዘመኔን
ድል ፡ በነሳው ፡ የሱስ ፡ ድልን ፡ ስላገኘው
ከንግዲህ ፡ ህይወቴ ፡ ላንተ ፡ መዘመር ፡ ነው
ባንተ ፡ ታሰበ ፡ የዘላለሜ ፡ ቀረ ፡ ባርነት ፡ ነፃ ፡ ሆንኩ ፡ እኔ
ዛሬ ፡ በደስታ ፡ እዘምራለው ፡ የሰማይ ፡ ዜጋ ፡ ወራሽ ፡ ሆኛለው
ወራሽ ፡ ሆኛለው ፡ ወራሽ ፡ ሆኛለው (፪x)
ወራሽ ፡ ሆኛለው ፡ ወራሽ ፡ ሆኛለው ፡ አሄ
ወራሽ ፡ ሆኛለሁ ፡ ልጅህ ፡ ሆኛለሁ
ይኸው ፡ በደስታ ፡ አንተን ፡ አመልካለው
ይሁንልህ ፡ ምስጋና ፡ ይሁንልህ ፡ ዝማሬ
ይሁንልህ ፡ አምልኮ ፡ ይሁንልህ ፡ ጌታዬ
ይሁንልህ ፡ ዕልልታ (፫x) ፡ ይሁንልህ ፡ ለጌታ
ይሁንልህ ፡ ምሥጋና ፡ ይሁንልህ ፡ ዝማሬ
ይሁንልህ ፡ አምልኮ ፡ ይሁንልህ ፡ ላምላኬ
ከሞት ፡ ድኛለሁና ፡ ከሞት ፡ ድኛለሁና ፡ ከሞት
ከሞት ፡ ድኛለሁና ፡ ላንተ ፡ ምስጋና

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists