Kishore Kumar Hits

Samuel Negussie - Ewedihalew lyrics

Artist: Samuel Negussie

album: Be'egziaber Alem, Vol. 1


የምወደው የምወደው ሁልጊዜ
ደስ የሚለኝ ደስ የሚለኝ እኔስ ሁሌ
የምወደው የምወደው ሁልጊዜ
ደስ የሚለኝ ደስ የሚለኝ እኔስ ሁሌ
ሳወራው ነው ሰው የመሆን ምክንያቴን
ሳወራው ነው የመዳኔን ምክንያቴን
ስለኔ በመስቀል ሞተሀል
እወድሃለሁ እወድሃለሁ
ስለኔ ደምህን አፍስሰሃል
እወድሃለሁ እወድሃለሁ
ስለእኔ ያልሆንከው የቱ ነው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ
ምክንያትህ ለኔ ያለህ ፍቅር ነው
እወድሃለሁ እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
እንዳንተ 'ሚሆንልኝ ማነው
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
ኢየሱስ ታሪኬን ቀየርከው
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
እንዳንተ 'ሚያስብልኝ ማነው
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
ዘላለሜ ያማረው ባንተ ነው
ተስፋ ያልነበረውን ያንን ሕይወቴን
የሞት ድምጽ ቢሰማ ጨለማው ቤቴ
በፍቅር ዘልቀህ ወደ ውስጠኛው ልቤ ውስጥ ገብተህ
አበራህልኝ የሕይወቴን ብርሃን ተስፋህን ሰተህ
ሰላምህ ሕይወቴን አጥለቀለቀው
የደስታህ ዘይት ውስጤን አራሰው
ዝም ብዬ አይደለም በጥዋት ማታ ኢየሱስ የምለው
ፍቅርህ ታሪኬን የሕይወቴን መሪር መልካም አርጎት ነው
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
እንዳንተ የሚመቸኝ ማነው
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
ኢየሱስ ታሪኬን ቀየርከው
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
ዘላለሜ ያማረው ባንተ ነው
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
እንዳንተ 'ሚያስብልኝ ማነው
የምህረት ልብ ለእኔ ያለህ
ሁሌ ሚጠብቀኝ ማይሰለቸኝ
ምክንያቱ ነው ከዘላለም ሞት ጥፋት መትረፌ
እንዲህ በሰላም እንዲህ በደስታ በሕይወት መኖሬ
ወደድከኝ ወደድከኝ እስከ ሞት ድረስ
ተሰቃየህልኝ ህመሜን ታመህ
ያን ሁሉ ስቃይ መራራ ጽዋ እንዲያ የጠጣኸው
ዛሬዬን አይተህ በእረፍት እንድኖር ነው እወድሃለሁ
ለኔ ነው ለኔ
ለኔ ነው ለኔ
ዛሬዬን አይተህ ሁሉን ታገስከው ኢየሱስ ወዳጄ
ለኔ ነው ለኔ
ለኔ ነው ለኔ
እወድሃለሁ ከሞት ያዳንከኝ አንተ ነህ ውዴ
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
እንዳንተ ሚሆንልኝ ማነው
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
ኢየሱስ ታሪኬን ቀየርከው
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
እንዳንተ ሚራራልኝ ማነው
እወድሃለሁ
እወድሃለሁ
እንዳንተ የታገሰኝ ማነው
ሰላሜ ነህ
ሰላሜ ነህ ሰላሜ
እረፍቴ ነህ
እረፍቴ ነህ በጣም የምወድህ
በጣም የምወድህ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists