Kishore Kumar Hits

Samuel Negussie - Be'egziaber Alem lyrics

Artist: Samuel Negussie

album: Be'egziaber Alem, Vol. 1


በእግዚአብሔር ዓለም (×፫)
ውድቀትና ክስረት አይታወቅም አይታወቅም
በእግዚአብሔር ዓለም (×፫)
ጨለማ ፈጽሞ አይታወቅም አይታወቅም
ሁሉ መልካም ነው ሁሉ መልካም
ሁሉ መልካም ነው መልካም ብቻ ነው
ሁሉ መልካም ነው ሁሉ መልካም
ሁሉ መልካም ነው መልካም ብቻ ነው
ለዚህ ነው በደስታ ለዚህ ነው በሆታ ምዘምረው
በአንተ ዓለም እየኖርኩ የኔን ዓለም ትቼ እንዲህ ምደሰተው
ለዚህ ነው በደስታ ለዚህ ነው በሆታ ምዘምረው
በአንተ ዓለም የሌለው በኔም ዓለም የለም ሁሌ እደሰታለው
በደስታ ዘምራለሁ
በእልልታ ዘምራለሁ
ሳላቋርጥ ዘምራለሁ
ባንተ ታስቢያለሁ
በደስታ ዘምራለሁ
በእልልታ ዘምራለሁ
ሳላቋርጥ ዘምራለሁ
ባንተ ታስቢያለሁ
ከእግዚአብሔር የሆነ ክፉ ነገር የለም የምን ሀዘን ጭንቀት
ሰላምና ደስታ በረከት ነው እንጂ የዘላለም እረፍት
ምድር ብትናወጥ ወደ ባህር ልብም ተራሮች ቢወርዱ
ከእግዚአብሔር ጋር ሆኜ በአንዳችም አልፈራም ህይወቴ ነው በእጁ
ሁሉ መልካም ነው ሁሉ መልካም
ሁሉ መልካም ነው መልካም ብቻ ነው
ሁሉ መልካም ነው ሁሉ መልካም
ሁሉ መልካም ነው መልካም ብቻ ነው
ለዚህ ነው በደስታ ለዚህ ነው በሆታ ምዘምረው
በአንተ ዓለም እየኖርኩ የኔን ዓለም ትቼ እንዲህ ምደሰተው
በደስታ ዘምራለሁ
በእልልታ ዘምራለሁ
ሳላቋርጥ ዘምራለሁ
ባንተ ታስቢያለሁ
ከዚህ ዓለም አይደለም ዘሬ መገኛዬ ታይቶ ከሚጠፋ
በእግዚአብሔር ቃል እንጂ ሁሉን በፈጠረ ሁሉን በሚያኖረው
ሁኔታን አይቼ ቀኑ ያላለኝን አልችልም አልልም
በእግዚአብሔር ዓለም ውስጥ በእሱ ለታመኑ ከባድ ነገር የለም
በእግዚአብሔር ዓለም (×፫)
ውድቀትና ክስረት አይታወቅም አይታወቅም
በእግዚአብሔር ዓለም (×፫)
ጨለማ ፈጽሞ አይታወቅም አይታወቅም
ሁሉ መልካም ነው ሁሉ መልካም
ሁሉ መልካም ነው መልካም ብቻ ነው
ሁሉ መልካም ነው ሁሉ መልካም
ሁሉ መልካም ነው መልካም ብቻ ነው
ለዚህ ነው በደስታ ለዚህ ነው በሆታ ምዘምረው
በአንተ ዓለም እየኖርኩ የኔን ዓለም ትቼ እንዲህ ምደሰተው
መዘመር ልምዴ ነው ማምለክ አንተን ብቻ
መቀኘት ለስምህ ሳለቋርጥ ጌታ
የደስታዬ ምንጩ የእረፍቴ መገኛ
አንተ ብቻ እኮ ነህ አንተ የኔ እረኛ
ደስተኛ ነኝ ደስተኛ
ደስተኛ ነኝ ደስተኛ
ደስተኛ ነኝ ደስተኛ
ደስተኛ ነኝ ደስተኛ
የደስታዬ ምንጩ የእረፍቴ ኢየሱስ ነው
አያቋርጥ ከቶ ሰላሜ ብዙ ነው
ደስታዬ ብዙ ነው
በደስታ ዘምራለሁ
በእልልታ ዘምራለሁ
ሳላቋርጥ ዘምራለሁ
ባንተ ታስቢያለሁ
በደስታ ዘምራለሁ
በእልልታ ዘምራለሁ
ሳላቋርጥ ዘምራለሁ
ባንተ ታስቢያለሁ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists