Kishore Kumar Hits

Samuel Negussie - Alresawum lyrics

Artist: Samuel Negussie

album: Be'egziaber Alem, Vol. 1


የብቸኝነቴ ወራት ወዳጄ
ሁሉም ገሸሽ ሲል ሲርቅ ከአጠገቤ
በመልካሙ ምክርህ በቃልህ ደግፈኸኝ
እዚህ ያደረስከኝ ኢየሱስ አንተ ነህ
አንተ ነህ የራራህልኝ
አንተ ነህ የተሸከምከኝ
አንተ ነህ ዘይት ቀብተህ
አንተ ነህ ፊትህ ያቆምከኝ
አንተ ነህ የደረስክልኝ
አንተ ነህ እኔን ያየኸኝ
አንተ ነህ ፈፅሞ አልረሳም
አንተ ነህ ሰው ያደረከኝ
ህልም ህልም ይመስለኛል ዞር ብዬ ሳየው
የትላንትናውን ያለፍኩት ባንተ ነው
አንተ ቀድመህ ፊቴ ባይቀና መንገዴ
እንዴት እሆን ነበር ለብቻዬ ባትራራልኝ ውዴ
ትላንትን አልፌ ዛሬ ላይ ስደርስ
ሁሉን እንዳለፍኩት በራሴ ብርታት
እኔ አይሆንልኝም ማሳየት እራሴን
ደብቄው ፍቅርህን ሰው የመሆን ምክንያቴን
ኢየሱስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም
ወዳጄ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም
እንደራራህልኝ እኔስ አልረሳውም
ብዙ እንደደገፍከኝ እኔስ አልረሳውም
እንደተሸከምከኝ እኔስ አልረሳውም
ፍቅር እንዳሳየኸኝ እኔስ አልረሳውም
በልቤ ተፅፎ ዘላለም ይኖራል
ፍቅር ምህረትህ የኔ ወዳጅ እንዴት ይረሳኛል
ፀጋህን አብዝተህ እየደጋገፍከኝ
ለአንዴም ሳይቀየር አባ ፊትህ ዛሬን አደረስከኝ
አይረሳም አይረሳም ኢየሱስ የዋልክልኝ
በእያንዳንዱ ህይወቴ አሻራህ አለብኝ
መልካምነትህን ሳወራ እኖራለው
ባንተ ሰው መሆኔን ፍጥረት ሁሉ ይስማው
ኢየሱስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም
ወዳጄ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም እኔስ አልረሳውም
እንደራራህልኝ እኔስ አልረሳውም
ብዙ እንደደገፍከኝ እኔስ አልረሳውም
እንደተሸከምከኝ እኔስ አልረሳውም
ፍቅር እንዳሳየኸኝ እኔስ አልረሳውም
አልረሳውም(2×)
እኔ አልረሳውም አልረሳውም
አልረሳውም(2×)
እኔ አልረሳውም አልረሳውም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists