Kishore Kumar Hits

Yohannes Girma - Amlake Destaye lyrics

Artist: Yohannes Girma

album: Amlake Destaye, Vol. 3


ከቶ እንበለስ ባያፍራ
ከወይንም ሃረግ ላይ ፍሬ ባይገኝ
የወይራ ሥራ ቢጐድል
እርሾችም መብልን ባይሰጡ
እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል
በመድኃኒቴ አምላክ ሃሴት አደርጋለሁ
ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያበረታ
በፍታዎች ላይ ያስኬደኛል (፪x)
አምላኬ ደስታዬ ደስታዬ ነህ
ኢየሱሴ ሙላቴ እርካታዬ ነህ (፪x)
በልጠኸኛል ሌላም አልፈልግም
ቀረም የምለው ነገርም የለኝ
ታምኜብህ በሁሉ ነገሬ
ይዤ መጣሁ የከንፈሬን ፍሬ (፪x)
ምን ይከብደው ብዬ ለየትኛው ልፍራ
ምን ያቅተውና ምኑን ብዬ ልፍራ (፪x)
ተራራ ላይ ማዳን የቻለው
ሸለቆው ውስጥ ኃይል የእርሱ ነው
ሁሉን የሚችል ሥሙ ኤልሻዳይ
የእኔ አምላክ ያለ በሰማይ (፪x)
እንደ እግዚአብሔር ያለ ከወዴት ይገኛል
የሕዝቡ መከታ ፅኑ ጋሻ ሆኗል (፪x)
መመኪያ ነው ለትውልድ ትምክህት
መጓደጃ የልጅ ልጅ ኩራት
የሚታመኑት ከፍ ከፍ ይላሉ
ለዘለዓለም ማዳኑን ያያሉ
ከቶ እንበለስ ባያፍራ
ከወይንም ሃረግ ላይ ፍሬ ባይገኝ
የወይራ ሥራ ቢጐድል
እርሾችም መብልን ባይሰጡ
እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለእኛል
በመድኃኒቴ አምላክ ሃሴት አደርጋለሁ
ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያበረታ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists