Kishore Kumar Hits

Bereket Tesfaye - Alehu lyrics

Artist: Bereket Tesfaye

album: Memihiru


አለሁ በምህረቱ አለሁ
በይቅርታው አለሁ
አለሁ ምህረት አግኝቻለው
እኔ ምን እሆናለው
አለሁ በምህረቱ አለሁ
እየማረኝ አለሁ
አለሁ ምህረት አጊኝቻለው
እኔ ምን እሆናለው
አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ
ምህረቱ ገኗል አለሁ
አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ
እኔ ምን እሆናለው
አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ
ምህረቱ ገኗል አለሁ
አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ
እኔ ምን እሆናለሁ

እነ ሚካኤል እነ ገብርኤል
እነ ሱራፌል እነ ኪሩቤል
በክፎቻቸው ተከልለውት
ፊቱ ሚቆሙለት አምላክ የሚሉት
በገራፊዎች ፊት ቆመልኝ እሱ ግን ስለኔ
ፍቅር ግድ ቢለው ሊያወጣኝ ከሀጢያት ከኩነኔ
ዙፋን የነበረው ከሰማይ ዳዊትን የረዳ
ተንከራተተልኝ እየሱስ ከናዝሬት ይሁዳ
ፍቅሩ ፈሰሰ ከምህረት ደጅ
እግዚአብሔር ከሰማይ ሰጠኝ አንድ ልጅ
ኑሮዬን ኑር አለኝ የኔን ልብስ ለበሰ
ቆሻሻ ህይወቴን በደሙ ቀደሰ
አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ
ምህረቱ ገኗል አለሁ
አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ
እኔ ምን እሆናለው
አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ
ምህረቱ ገኗል አለሁ
አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ
እኔ ምን እሆናለሁ

ይሁን በምትል ቃል ፍጥረትን የሰራ
ጥበብ የሻተውን ጥበብን ያስወራ
አባቶች ሲጠሩት በእሳት የመለሰ
እረኛው ዳዊትን ተናግሮ ያነገሰ
እንደሚታረድ በግ ዝም አለ ስለኔ እየሱስ
ፍቅርን የኖረ በተግባር የፍቅር ንጉስ
ምድርን ያቆመ በቃሉ ያለ አንዳች ምሶሶ
እሱ ግን ዝም አለ ሞተልኝ የኔን ውርደት ለብሶ
ፍቅሩ ፈሰሰ ከምህረት ደጅ
እግዚአብሔር ከሰማይ ሰጠኝ አንድ ልጅ
ኑሮዬን ኑር አለኝ የኔን ልብስ ለበሰ
ቆሻሻ ህይወቴን በደሙ ቀደሰ
አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ
ምህረቱ ገኗል አለሁ
አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ
እኔ ምን እሆናለው
አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ
ምህረቱ ገኗል አለሁ
አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ
እኔ ምን እሆናለሁ
አለሁ በምህረቱ አለሁ
በይቅርታው አለሁ
አለሁ ምህረት አግኝቻለው
እኔ ምን እሆናለው
አለሁ በምህረቱ አለሁ
እየማረኝ አለሁ
አለሁ ፍቅሩን ቀምሻለው
እኔ ምን እሆናለው
አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ
ምህረቱ ገኗል አለሁ
አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ
እኔ ምን እሆናለው
አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ
ምህረቱ ገኗል አለሁ
አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ
እኔ ምን እሆናለው

አብ ከላይ ሆኖ ለኔ ራራልኝ አዘነ
ሊያድነኝ ሽቶ አንድ ልጁ ላይ ጨከነ
ፍቅር ልሂድ አለ ታዘዘ ለአባቱ
ክብሩን ትቶ ወርዶ አዳነኝ በሞቱ
ፍቅር እንደ እየሱስ የለም
ፍቅር እንደ እየሱስ የለም
ፍቅር እንደ እየሱስ የለም
ፍቅር እንደ እየሱስ የለም
ፍቅር (እንደ እየሱስ የለም)
ፍቅር (እንደ እየሱስ የለም)
ፍቅር (እንደ እየሱስ የለም)
ፍቅር (እንደ እየሱስ የለም)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists