Kishore Kumar Hits

Bereket Tesfaye - Maranata lyrics

Artist: Bereket Tesfaye

album: Memihiru


የመምጣትህ ነገር የመጨረሻው
የነገርከን ትንቢት እየሆነ ነው
ናፍቆቱ አስባለንኝ አሜን ማራናታ
ላይህ ጓጉቻለው ኢየሱስ የኔ ጌታ
ጌታ ኢየሱስ አትመጣም ወይ
የደማልኝን ጎንህን ልይ
አንተን ለማየት አይኖቼ ሻቱ
ቶሎ ናልኝ ኢየሱስ የናዝሬቱ
ካንተ ጋር ልዋል ካንተ ጋል ልደር
እንደ ዮሕንስ በደረትህ ስር
ደስታዬ የምለው ትልቁ እርካታዬ
አንተ ያለህበት ስኖር ነው ጌታዬ
በሌለህበት ከማገኝ ድሎት
ምድረበዳ ላይ ካንተ ጋር ልሰንብት
አንተን የማየት ናፍቆት ገባብኝ
እንደጓጓሁኝ መች አቀራለሁኝ
ከአመጻ ብዛት ፍቅር ቀዘቀዘ
ሰው ወንድሙን ገሎ መቼ ተወቀሰ
አመጸኞች በዙ ክፋቱ ጨምሮ
ተላልፈው ተሰጡ ለማይረባ ዐዕምሮ
የድኆች ዳኛ የሁሉ አለቃ
ናና ከልከለው ለቅሶአችን ይብቃ
የናቶች እንባ ይላል ዋይ ዋይ
ሩህሩህ ጌታ አትመጣም ወይ
ቤተ ክርስቲያን ተነሺና አብሪ
ፍቅርን ለጣሉ እንዳዘምሪ
የገሃነም ደጅ ለካ ጥላቻ ነው
ማይቋቋምሽ ሰይፍሽ ፍቅር ሲሆን ነው
ጦር መሳሪያውን ፍቅር ያደረገ
ጠላቱን ረቶ ወንድም አደረገ
የሰው ጠባብ አፍ የሚጎርስ እህል
ክፉ አንደበት አክሎአል ሲኦል
አትመጣም ወይ (ማራናታ)
አናርፍም ወይ (ማራናታ)
አትመጣም ወይ (ማራናታ)
አናርፍም ወይ (ማራናታ)
(ና ና ና ና ና ማራናታ)
(ና ና ና ና ና ማራናታ)
(ና ና ና ና ና ማራናታ)
(ና ና ና ና ና ማራናታ)
ሃሳቢ መምህራን ነብያቶች በዙ
ተናገረኝ ባዮች ለገንዘብ የተገዙ
ለታመመው ምስኪን የእንግዳ ማረፊያ
በሽታው ሳያንሰው በፀሎት ሰበብ ዝርፊያ
ደምህ ተረግጦ ገንዘብ ገነነ
አንተን ያወቀ ሰው ክፉ ሆነ
ነዋይ ሚያፈቅር ትውልድ ተነሳ
ያረግክለትን ምህረት የረሳ
ፈውሱ ለታይታ ለንግድ ቀረበ
በአዳኙ ስም ገንዘብ ተሰበሰበ
ገበያው ደርቶ በወንጌል ሰበብ
ስንቱን ታዘብነው አወይ ጉድ አጀብ
በሰጠው ጸጋ የሆነ ነጋዴ
በፍርድ ቀን የሚል ነው ወይኔ ጉዴ
መምጣቱ አይቀርም የእረኞች አለቃ
ስለ በጎቹ የሚራራ ጠንቃቃ
አትመጣም ወይ (ማራናታ)
አናርፍም ወይ (ማራናታ)
አትመጣም ወይ (ማራናታ)
አናርፍም ወይ (ማራናታ)
(ና ና ና ና ና ማራናታ)
(ና ና ና ና ና ማራናታ)
(ና ና ና ና ና ማራናታ)
(ና ና ና ና ና ማራናታ)
ወደ ዐለም ሂዱ ወንጌልን ሰብኩ
ነበር የተባልነው መስክሩ ታደጉ
ሰው ግን ካስማ ሰርቶ ወንበሯን ወደደ
መምህር እና ጌታ መባልን ለመደ
ወንጌል እንስራ አንቱታው ቀርቶ
ይሽለም የል ወይ የሰራ ተግቶ
ከታበይንበት ዙፋናችን
እስኪ እንውረድ ለጌታችን
አላወጣንም አጋንንቶችን?
አልፈወስንም ወይ በሽተኞችን?
ጌታ በስምህ ብዙ አድርገን
አላውቃችሁም ስለምን አልከን?
ከሚሉት ወገን እንዳይሆን ህይወቴ
መብራቴን ላብራ ሳይጎድል ዘይቴ
እስከምትመጣ ወይ እስክትወስደኝ
እየጠበኩኝ እጸናለሁኝ
(ና ና ና ና ና ማራናታ)
(ና ና ና ና ና ማራናታ)
(ና ና ና ና ና ማራናታ)
(ና ና ና ና ና ማራናታ)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists