Kishore Kumar Hits

Bereket Tesfaye - Menifesih lyrics

Artist: Bereket Tesfaye

album: Live


እንጨት ፡ እና ፡ ውኃ ፡ በሌለበት ፡ ቦታ
ናፈቅከኝ ፡ ጌታ ፡ ናፈቅከኝ ፡ ጌታ (፪x)
ትርጉም ፡ ባለበት ፡ የውኃ ፡ ጠብታ
ግን ፡ ነፍሴ ፡ ጮኽች ፡ አንተን ፡ ተጠምታ
አምላኬ ፡ አንተ ፡ ዘንድ ፡ እገሰግሳለው
ክብርህን ፡ ለማየት ፡ እናፍቃለው (ኦኦው)
መንፈስህን (፬x)
ወደዋለው ፡ መንፈስህን
ተጠምቻለው ፡ መንፈስህን
መንፈስህን (፬x)
ወደዋለው ፡ መንፈስህን
ተጠምቻለው ፡ መንፈስህን
ህልውናህ ፡ ለእኔ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው
መገኘትህ ፡ ለእኔ ፡ የነፍሴ ፡ ደስታ ፡ ነው
እጠማሃለው (፪x)
እወድሃለው (፪x)
ስንዘምር ፡ አንተን ፡ ስንጠራ
በጉባያችን ፡ ክብርህ ፡ ሲገባ
ያለሁ ፡ መሰለኝ ፡ መንግሥተ ፡ ሰማይ
መገኘትህን ፡ በመንፈሴ ፡ ሳይ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists