Kishore Kumar Hits

Bereket Tesfaye - Betamrat lyrics

Artist: Bereket Tesfaye

album: Leekea Kahinea, Vol.1


ለኔ ቀኑ ጨልሞ መስማት እንጂ ማየት አልችል
ጥዋት ልለምን የወጣው
መሽቶ በሰው ነው ምገባው
ትልቅ ትንሽ መሪዬ
የሰው ፈቃድ ማደሪያዬ
የእድሜዬን ግማሽ ቆጠርኩት
ጨለማውን ለመድኩት
መጣ ኢየሱስ ይህ የዓለም ብርሃን
ዓይኖቼን ከፈተ በእውርነቴ ሀገር ታሪኬ ተለወጠ
መጣ ኢየሱስ ይህ የዓለም ብርሃን
ዓይኖቼን ከፈተ በእውርነቴ ሀገር ታሪኬ ተለወጠ
የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ ተከፈተ ብርሃኔ
መልካምነቱን አየሁኝ በዚች በአጭሯ ዘመኔ

ተጥዬ የነበርኩኝ ያ ምስኪኑ እኔ ነኝ
መንገደኛ የማያየኝ አሳዛኝ ሰው ነበርኩኝ
በሀጢያቱ ወደቀ በእግዚአብሔር ደቀቀ
ብለው ሰዎች ፈረዱ
ስብራቴን ሳይረዱ
ደጉ ጌታ ከሰማይ አየኝ
ከውድቀቴ አነሳኝ
ቁስሌን ፈውሶ
አከበረኝ መልሶ
ደጉ ጌታ ከሰማይ አየኝ
ከውድቀቴ አነሳኝ
ቁስሌን ፈውሶ
አከበረኝ መልሶ
በታምራት የሚያኖረኝ
አምላክ አለኝ ሚያስብልኝ
የመቆሜ ምክንያቱ
የእግዚአብሔር ምህረቱ

በአልጋዬ ላይ ተኝቼ
ለዓመታት ሸትቼ
መልአኩ ሲያናውጠው
ማን ሊከተኝ ወደ ውሃው
ዘመድ አዝማድ የሌለኝ
የኔ ምለው ሚረዳኝ
ቀርቦ ችግሬን አየና
ተራመድ ሂድ ተነሳና
ያለው ጌታ ለካስ ዘመዴ ነው
ስለኔ ሚሰማው
ሽባነቴን ሽሮ
አቆመኝ ቀይሮ
ያለው ጌታ ለካስ ዘመዴ ነው
ስለኔ ሚሰማው
ሽባነቴን ሽሮ
አቆመኝ ቀይሮ
በታምራት የሚያኖረኝ
አምላክ አለኝ ሚያስብልኝ
የመቆሜ ምክንያቱ
የእግዚአብሔር ምህረቱ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists