Kishore Kumar Hits

Bereket Tesfaye - Befersew lyrics

Artist: Bereket Tesfaye

album: Leekea Kahinea, Vol.1


የእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ ፈርሶ
መሠዊያው ፡ ተድበስብሶ
የእራስህን ፡ ቤት ፡ ትሰራለህ
ስለ ፡ ወንጌል ፡ አይገድህ
በፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ማን ፡ ይቆማል
ሁሉ ፡ የራሱን ፡ ድንጋይ ፡ ይክባል
በፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ማን ፡ ይቆማል
ኤሎሂ ፡ ማን ፡ ይሻለናል?
እግዚአብሔር ፡ ወይ ፡ ትውልድ ፡ አስነሳ
ስለ ፡ ቤትህ ፡ የሚሳሳ
ግድ ፡ የሚለው ፡ የወንጌል ፡ ነገር
በጥቅም ፡ የማይጭበረበር
ኤሎሂ (፫x) ፡ ፡ አሃ ፡ ኤሎሂ
የቀደሙት ፡ ሃዋሪያት ፡ ነቢያት
ራሳቸውን ፡ ሰጡ ፡ እስከሞት ፡ ድረስ
ዛሬ ፡ ራሱን ፡ ሚሰጥ ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ማነው
የወንጌሉ ፡ ቅናት ፡ ውስጡን ፡ የበላው
እግዚአብሔር ፡ ወይ ፡ ትውልድ ፡ አስነሳ
ስለ ፡ ቤትህ ፡ የሚሳሳ
ግድ ፡ የሚለው ፡ የወንጌል ፡ ነገር
በጥቅም ፡ የማይጭበረበር
ወንድም ፡ ለወንድሙ ፡ ማዘን ፡ ሲገባዉ
ባደባባይ ፡ ላይ ፡ ክስ ፡ ዝንተላዉ ፡ ምንድን ፡ ነው
እውነቱ ፡ ከተቀየረማ ፡ ከቀለላ ፡ ዋጋው ፡ ክርስትና
ምንድን ፡ ነው ፡ የሚሻለን ፡ ኤሎሂ ፡ መፍትሄ ፡ ስጠን
እግዚአብሔር ፡ ወይ ፡ ትውልድ ፡ አስነሳ
ስለ ፡ ወንድሙ ፡ የሚሳሳ
ግድ ፡ የሚለው ፡ የፍቅር ፡ ነገር
በውሸት ፡ የማይወነጅል
ኤሎሂ (፫x) ፡ አሃ ፡ ኤሎሂ
ትውልድ ፡ ሲተራመስ ፡ በራሱ ፡ መንገድ ፡ ላይ
ግማሹ ፡ ወደታች ፡ ግማሹ ፡ ወደላይ
ወዴት ፡ እንደምሄድ ፡ ትውልድ ፡ አላወቀም
የዛሬን ፡ እንጂ ፡ የነገን ፡ አላየም (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ሰው ፡ አስነሳልን
መንገድህን ፡ የሚያሳየን
ቃልህን ፡ ብቻ ፡ የሚናገር
በሁኔታ ፡ የማይጭበረበር
ኤሎሂ (፬x)
የቀደሙት ፡ ሃዋሪያት ፡ ነቢያት
ራሳቸውን ፡ ሰጡ ፡ እስከሞት ፡ ድረስ
ዛሬ ፡ ራሱን ፡ ሚሰጥ ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ማነው
የወንጌሉ ፡ ቅናት ፡ ውስጡን ፡ የበላው
እግዚአብሔር ፡ ወይ ፡ ትውልድ ፡ አስነሳ
ስለ ፡ ቤትህ ፡ የሚሳሳ
ግድ ፡ የሚለው ፡ የወንጌል ፡ ነገር
በጥቅም ፡ የማይጭበረበር
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ሰው ፡ አስነሳልን
መንገድህን ፡ የሚያሳየን
ቃልህን ፡ ብቻ ፡ የሚናገር
በሁኔታ ፡ የማይጭበረበር
ኤሎሂ (፬x)
የእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ ፈርሶ ፣ መሠዊያው ፡ ተድበስብሶ
የእራስህን ፡ ቤት ፡ ትሰራለህ ፣ ስለ ፡ ወንጌል ፡ አይገድህ
በፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ማን ፡ ይቆማል
ሁሉ ፡ የራሱን ፡ ድንጋይ ፡ ይክባል
በፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ማን ፡ ይቆማል
ኤሎሂ ፡ ማን ፡ ይሻለናል?
እግዚአብሔር ፡ ወይ ፡ ትውልድ ፡ አስነሳ
ስለ ፡ ቤትህ ፡ የሚሳሳ
ግድ ፡ የሚለው ፡ የወንጌል ፡ ነገር
በጥቅም ፡ የማይጭበረበር
ኤሎሂ (፫x) ፡ አሃ ፡ ኤሎሂ
ኤሎሂ (፫x) ፡ አሃ ፡ ኤሎሂ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists