Kishore Kumar Hits

Pamfalon - Mistrawi lyrics

Artist: Pamfalon

album: 11/11/11


እሺ ብሎ መቀበልን ቃል ለቃል
ብቻ ግን አሁን ወንድም አለም
እያወቅን ቃል ተቀባይም እንሁን
አዋቂነት ነው ብለው አሳወቁን ዘንድሮ
የሰው ልጅን ማፋጠጥ አÃዋጣም ዘንድሮ
ስሜት መጠበቅ ባንዱ አይን
ከጅ ወደ አፍ ላለው ሌላ
አስመስሎም ማሳለፍ
ሆኑዋል ሁላችንም ላይ ባይ
በጎ መስሎኝ በኔ ኤይን
ሀቅ ሚሉዋትን ማሳደድ
ከወዳጅም አፋታኝ ዘጋብኝ
ብዙ መንገድ
መስማት ከሚፈልገው በላይ
ስው ከነገርከው ጠላት መባል
እንደሚችል ቀድመህም እወቀው
አውቃለው እራሴም ምን ማለት እንደሆነ
ከሌላ ስው መካፈል አልፈልገውም ሲኖር
ስልኬንም አለማንሳት የለም በልልኝ ማስባል
ሚስጥራዊነቴ
የሰወረኝም ባካል
የት ነው ጸባይ ምንጭም
ልየው ብዬ ሳሰላስል
ሚስጥሬን ለመፋታት ነው ማረገው
ይሔን ጥረት
እኔን ብቻ መስሎኝ ነበረ
ሚስጥር በዛብኝ አረ ከበደኝ
ለማን ልናገር ማንስ ይፍታኝ
ሚስጥራዊነቱስ አላዋጣኝ(2)

ይሄ ነገር ከባህል ነውስ የተገናኘው
ፈረንጁስ ሚስጥር አለው
የኛሰው ብቻ ነው ወይ
ሰው ሚስቱ እንዳረገዘች
ደብቆም ዘጠኝ ወር
ክርስትና ሲጋብዝ ግራ ሳያጋባው ነውወይ
ንጉስ ቤት ተፈጽሞም ከንጉስ ቤት
አይወታም አይነት ነገር ቢመስልም
እንደ እውነት አያረካም
ይሉኝታ የሚሉት ነገር
ነው የዚ መሰረት
መስሎ ከመገኘት በላይ
እሴት ያገኘበት
ብሄረሰባዊ ጫና
ወይንስ ባህል የሚሉት
ለህዝባችን ክፋት ሆኑዋል
አንዱ ነኝ እስከሚሉት
ምእራባዊያን ባይመቹኝም
ግን በዚ ይመቻቸው
ወደገደለው ወዲያው
ዳር ዳሩም አይመቻቸው
ሁሉን ሰው ማስደሰት ግን
ምን ጊዜም ስንፈልግ
ሚስጥራችንም ለወዳጅ ይጨምራል በልክ
እውነት ትሰጣለችም ግን ሀይል
ትላለችም ደግፍ
ላባዬ ረግፎ ሳያልቅ
ልብረርበትም በልክ
እኔን ብቻ መስሎኝ ነበረ
ሚስጥር በዛብኝ አረ ከበደኝ
ለማን ልናገር ማንስ ይፍታኝ
ሚስጥራዊነቱስ አላዋጣኝ(5)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists