Kishore Kumar Hits

Girma Tefera Kassa - Fiqir Bemetenu lyrics

Artist: Girma Tefera Kassa

album: Gin Yet Hager


በእውነተኛ ስሜት አስበሽ በመንፈስ
በመጠኑ አፍቅሪኝ ብዙ ዘመን ድረስ
እፍ'ፍ ያሉት ፍቅር የያዙት ቸኩሎ
በጣም ይግልና ይጠፋል ተቃጥሎ
ይጠፋል ተቃጥሎ

ፍቅር የሰውን ልጅ ሲይዝ በዝግታ
ጠንካራ ይሆናል በመላላት ፋንታ
የችኮላ ነገር አያስተማምንም
ፍቅሬ ፍቅሬ ስላልሽ እውነት አይመስለኝም
እውነት አይመስለኝም

መች ወዲያው ይነጋል መቼስ ወዲያው መሽቶ
ሰኔ አይታጨድም ሰኔ ላይ ተዘርቶ
እንዲህ ነው ተፈጥሮ ሂደት አለው ሁሉ
ዘመን እንዲኖረው ይሁን በመጠኑ
ፍቅር በመጠኑ
እንዳይሰናከል ባጭሩ
መድረሻው እንዲያምር ጅምሩ
ሰከን ማለት ነው ሚስጥሩ
ተጠብቆ እንዲኖር ውበቱ
አስደሳች እንዲሆን ስሜቱ
ያስፈልጋል ረጋ ማለቱ

በእውነተኛ ስሜት አስበሽ በመንፈስ
በመጠኑ አፍቅሪኝ ብዙ ዘመን ድረስ
እፍ'ፍ ያሉት ፍቅር የያዙት ቸኩሎ
በጣም ይግልና ይጠፋል ተቃጥሎ
ይጠፋል ተቃጥሎ
በጣም ትንሽ ሳይሆን በጣምም ሳይበዛ
ፍቅርን ሲመጥኑት አለው ትልቅ ለዛ
ስለዚህ ውደጂኝ በእውነተኛ መንፈስ
እንዳትለዋወጭ ብዙ ዘመን ድረስ
ብዙ ዘመን ድረስ

ፍቅር የበዛ እንደው ኪሎው ይካበዳል
አውቀው በመጠኑ ቢያደርጉት ይሻላል
እውነተኛን ስሜት ፈላጊዎች ብትሆኑ
ፍቅር ጠቃሚ ነው ሲሆን በመጠኑ
ሲሆን በመጠኑ
ፍቅር ጠቃሚ ነው ሲሆን በመጠኑ
ሲሆን በመጠኑ
እንዳይሰናከል ባጭሩ
መድረሻው እንዲያምር ጅምሩ
ሰከን ማለት ነው ሚስጥሩ
ተጠብቆ እንዲኖር ውበቱ
አስደሳች እንዲሆን ስሜቱ
ያስፈልጋል ረጋ ማለቱ
እንዳይሰናከል ባጭሩ
መድረሻው እንዲያምር ጅምሩ
ሰከን ማለት ነው ሚስጥሩ
ተጠብቆ እንዲኖር ውበቱ
አስደሳች እንዲሆን ስሜቱ
ያስፈልጋል ረጋ ማለቱ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists