Kishore Kumar Hits

Girma Tefera Kassa - Min Wuyelish lyrics

Artist: Girma Tefera Kassa

album: Gin Yet Hager


ምን
ምን ውዬልሽ ይሆን
ምን አድርጌልሽ
ስታሞጋግሺኝ
ውለሽ ማደርሽ
ያንቺስ መልካምነት
መች ያልቃል ተቆጥሮ
መፅሐፍ ይወጣዋል
ቢፃፍ ተዘርዝሮ
እንዲያው ምን
ምን ውዬልሽ ይሆን
ምን አድርጌልሽ
ስታሞጋግሺኝ
ውለሽ ማደርሽ
ያንቺስ መልካምነት
መች ያልቃል ተቆጥሮ
መፅሐፍ ይወጣዋል
ቢፃፍ ተዘርዝሮ
እሩቅ ጥልቁ ፍቅርሽ
ፅናት ትዕግሥትሽ
ቅንነት ደግነት
ታማኝነትሽ
እንደሷ አይነት ፍጡር
አለች ወይ እስኪባል
ስላንቺ ሲነገር
ሰው ሁሉ ጉድ ይላል
ጤና ይስጥሽ እንጂ
እድሜሽን አርዝሞ
እኔ ያንቺን ውለታ
አልከፍልም ፈፅሞ
ጤና ይስጥሽ እንጂ
እድሜሽን አርዝሞ
እንቅፋት አይንካሽ
አንቺንስ ፈፅሞ
ሰላም ሁኚልኝ
ሁኚልኝ
ደህና ሁኚልኝ
ሁኚልኝ
ሁሌም በደስታ ኑሪልኝ
አትከፊብኝ
ሰላም ሁኚልኝ
ሁኚልኝ
ደህና ሁኚልኝ
ሁኚልኝ
ሁሌም በደስታ ኑሪልኝ
ሳትከፊብኝ
ምን
ምን ውዬልሽ ይሆን
ምን አድርጌልሽ
ስታሞጋግሺኝ
ውለሽ ማደርሽ
ያንቺስ መልካምነት
መች ያልቃል ተቆጥሮ
መፅሐፍ ይወጣዋል
ቢፃፍ ተዘርዝሮ
ትሁትነትሽን
ለማንም አልሰጠው
ሊያስተምርብሽ ነው
አንቺን የመረጠው
አሁን ባለንበት
በሚታማው ዘመን
ያንቺ አይነቱን ያብዛው
ብሎ ነው መለመን
ጤና ይስጥሽ እንጂ
እድሜሽን አርዝሞ
እኔ ያንቺን ውለታ
አልከፍልም ፈፅሞ
ጤና ይስጥሽ እንጂ
እድሜሽን አርዝሞ
እንቅፋት አይንካሽ
አንቺንስ ፈፅሞ
ሰላም ሁኚልኝ
ሁኚልኝ
ደህና ሁኚልኝ
ሁኚልኝ
ሁሌም በደስታ ኑሪልኝ
አትከፊብኝ
ሰላም ሁኚልኝ
ሁኚልኝ
ደህና ሁኚልኝ
ሁኚልኝ
ሁሌም በደስታ ኑሪልኝ
አትከፊብኝ
ሰላም ሁኚልኝ
ሁኚልኝ
ደህና ሁኚልኝ
ሁኚልኝ
ሁሌም በደስታ ኑሪልኝ
ሳትከፊብኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists