Kishore Kumar Hits

Girma Tefera Kassa - Menta Wubet lyrics

Artist: Girma Tefera Kassa

album: Gin Yet Hager


ቀኔን ምሽቴን የምታደምቂ
ልቤን በፍቅርሽ የምታሞቂ
ግማሽሽ ጨረቃ ግማሽ ፀሃይ
ካንድም ሁለት ነው ተፈጥሮሽን ሳይ
ግማሽሽ ጨረቃ ግማሽ ፀሃይ
መንታ ዉበት አለሽ ከሁልም የሚለይ
ሙቀት እና ብርሃን እኩል አጣምሮ
በሚያስደምም ጥበብ ሴት አሳምሮ
ከዚ በፊት ፈጥሮ አያውቅም ሌላ
ወደፊትም እንጃ ከዚም በሁዋላ ከዚም በሁዋላ
ሙቀት እና ብርሃን እኩል አጣምሮ
በሚያስደምም ጥበብ ሴት አሳምሮ
ካልቺ በፊት ፈጥሮ አያውቅም ሌላ
ወደፊትም እንጃ ከዚም በሁዋላ ከዚም በሁዋላ
ሙቀት ነሽ ድምቀት ለምድር ለሰማይ
ጨረቃም እና ፀሃይ ሁለቱን መሳይ
ባለ መንታ ዉበት ሁሉን አማላይ
እንዳንቺማ የለም በዚች አለም ላይ
ቁንጅና ባንቺ ላይ በርታ የኔ ፀሃይ የኔ ብርሃን
ቁንጅና ባንቺ ላይ በርታ የኔ ፀሃይ የኔ ብርሃን
ቀኔን ምሽቴን የምታደምቂ
ልቤን በፍቅርሽ የምታሞቂ
ግማሽሽ ጨረቃ ግማሽ ፀሃይ
ካንድም ሁለት ነው ተፈጥሮሽን ሳይ
ግማሽሽ ጨረቃ ግማሽ ፀሃይ
መንታ ዉበት አለሽ ከሁልም የሚለይ
መቼም ይሁን የትም የአዳም ልጅ ሁሉ
እያየሽ ይራዳል የሰራ አካሉ
ደካማው ከብቱ መች ይለይ እና
ይሸበራል ልቡ ባንቺ ቁንጅና ባንቺ ቁንጅና
በቁንጅና ሚዛን ሲጨቃጨቅ ኖሮ
አብዛኛው ሰው ባንቺ ተስማምቷል ዘንድሮ
የኔ ልዩ መብራት የአይኖቼ ሲሳይ
የትም የለም እና ከቶ አንቺን መሳይ
ቁንጅና ባንቺ ላይ በርታ የኔ ፀሃይ የኔ ብርሃን
ቁንጅና ባንቺ ላይ በርታ የኔ ፀሃይ የኔ ብርሃን
ቁንጅና ባንቺ ላይ በርታ የኔ ፀሃይ የኔ ብርሃን
ቁንጅና ባንቺ ላይ በርታ የኔ ፀሃይ የኔ ብርሃን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists