Kishore Kumar Hits

Girma Tefera Kassa - Min Waga Alew lyrics

Artist: Girma Tefera Kassa

album: Gin Yet Hager


ወደ ሗላ ሄዶ ያንን ላይመልሰው
የትናንቱ ትውልድ የዛሬን ቢወቅሰው
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ወደ ሗላ ሄዶ ያንን ላይመልሰው
የትናንቱ ትውልድ የዛሬን ቢወቅሰው
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ለመራራም ይሁን ለጣፋጩም ፍሬ
የትናንቱ ችግር ምክናያት ነው ለዛሬ
ቅጥጥል ነው እና የትውልድ ጉዞ
የዛሬው ነገ ይወልዳል አርግዞ
ምርቃቱን ያሰማን አይጠቅመንም እርግማን
ማመስገን ማድነቅን ዛሬም እስካላወቅን
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ዘመን ሲነሳ ሁሌም ወቀሳ
ዘመን ሲነሳ ሁሌም ወቀሳ
ያደፈርሳል ንጹን ፍቅር ይቅር ይቅር ወቀሳው ይቅር
የፊተኛው አልፎ የሁዋላው ሲተካ
ሁልም ባንድ ሚዛን አይችልም ሊለካ
ተግባሩ ሲመዘን ቢለይም መጠኑ
የራሱ ልክ አለው ሁልም በዘመኑ
ያኛው መሰረት ጥሎ ይሄኛው አስቀጥሎ መጪው እንዲጨርሰው
ፍቅሩን ካላረሰ
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ወደ ሗላ ሄዶ ያንን ላይመልሰው
የትናንቱ ትውልድ የዛሬን ቢወቅሰው
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ሰጪም ተቀባይም በየበኩላቸው
በቅደም ተከተል ድርሻ ድርሻ አላቸው
ሰጪም በሰጠው ልክ ከተመዘነበት
ያጎደለው ካለ እሱም እዳ አለበት
ሁልም ራሱን መርምሮ
ከስተቱ ተምሮ
ዛሬን የቀየረው ነገን ካላሳመረው
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
ታሬክ ሲወሳ ትውልድ ወቀሳ
ታሬክ ሲወሳ ትውልድ ወቀሳ
ያቀዘቅዛል የሞቀን ፍቅር ይቅር ይቅር ወቀሳንው ይቅር
ዘመን ሲነሳ ሁሌም ወቀሳ
ዘመን ሲነሳ ሁሌም ወቀሳ
ያደፈርሳል ቀጣዩን ፍቅር ይቅር ይቅር ወቀሳንው ይቅር

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists