Kishore Kumar Hits

Girma Tefera Kassa - Enderase lyrics

Artist: Girma Tefera Kassa

album: Gin Yet Hager


አንቺን እንደ ራሴ
ልወድሽ
ላፈቅርሽ
በሙሉ ስሜቴ
ፍፁም ላልለይሽ
ከጎንሽ ላልርቅሽ
እስከ እለተ ሞቴ
እንደአይኔ ብሌን እንዳይሽ እንዳ'ይኔ
ልንከባከብሽ ነው የወሰንኩት እኔ
ላምንሽ እንደራሴ
ልወድሽ
ላፈቅርሽ
በሙሉ ስሜቴ
ፍፁም ላልለይሽ
ከጎንሽ ላልርቅሽ
እስከ እለተ ሞቴ
እንደአይኔ ብሌን እንዳይሽ እንዳ'ይኔ
ልንከባከብሽ ነው የወሰንኩት እኔ
በፍቅሬ እምነት ኖሮሽ
ሳትጠራጠሪ
ከሀሳብ ከጭንቀት
ርቀሽ እንድትኖሪ
አቅሜ የፈቀደውን
ሁሉ ላደርግልሽ
መቼም በማላጥፈው
ቃሌ ቃል ልግባልሽ
እጥፍ ይሆናል ደስታዬ
ተደስተሽልኝ ሳይ
ይሄ እኮ ነው ፍላጎቴ
ስኖር በዚህች አለም ላይ
አላጥፈውም ይሄን ቃሌን
እመኚብኝ አከብራለሁ
ቀን ሌትም ሳልለይሽ
ሁሌ አብሬሽ እኖራለሁ
አንቺን እንደ ራሴ
ልወድሽ
ላፈቅርሽ
በሙሉ ስሜቴ
ፍፁም ላልለይሽ
ከጎንሽ ላልርቅሽ
እስከ እለተ ሞቴ
እንደአይኔ ብሌን እንዳይሽ እንዳ'ይኔ
ልንከባከብሽ ነው የወሰንኩት እኔ
የተለመደ ነው
ሰው ለራስ መኖሩ
ከዚያም ያልፋል እንጂ
የፍቅር መስመሩ
ከራሴ ፍላጎት
ያንቺን አስቀድሜ
ልኖር ወስኛለሁ
እስካለሁ በቁሜ
እጥፍ ይሆናል ደስታዬ
ተደስተሽልኝ ሳይ
ይሄ እኮ ነው ፍላጎቴ
ስኖር በዚህች አለም ላይ
አላጥፈውም ይሄን ቃሌን
እመኚብኝ አከብራለሁ
ቀን ሌትም ሳልለይሽ
ሁሌ አብሬሽ እኖራለሁ
እጥፍ ይሆናል ደስታዬ
ተደስተሽልኝ ሳይ
ይሄ እኮ ነው ፍላጎቴ
ስኖር በዚህች አለም ላይ
አላጥፈውም ይሄን ቃሌን
እመኚብኝ አከብራለሁ
ቀን ሌትም ሳልለይሽ
ሁሌ አብሬሽ እኖራለሁ
እጥፍ ይሆናል ደስታዬ
ተደስተሽልኝ ሳይ
በቃይሄ ነው ፍላጎቴ
ስኖር በዚህች አለም ላይ
አላጥፈውም ይሄን ቃሌን
እመኚብኝ አከብራለሁ
ቀን ሌትም ሳልለይሽ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists