Kishore Kumar Hits

Girma Tefera Kassa - Dezi Derata lyrics

Artist: Girma Tefera Kassa

album: Gin Yet Hager


እሰይ እንኩዋን
እንኩዋን ራሴን ሆንኩኝ ከምንም በላይ
ባምሳል የፈጠረኝ ለዚ አይደለል ወይ
ደስተኛ ሆኛለው በሂወቴ
በዚ ማንነቴ
አልቃጣም ሌላውን ልመስል ያልሰጥኝን ይመስል
ሰው ሆይ በዚች በጥድፊያ አለም
ጸንተህ እንድትኖር በርጋታ
ሁሌም ልብህን ተከተል ይላል ህገ ዴዝ ዴራታ
ሰው ይበላል እና ያንደበቱን ፍሬ
በመሸበት እደር እውነት ተናግሬ
እኔ ላይ ቢሆንም የማልፈልገውን
በሌላው ላይ እንዳላደርግ ስጠኝ ልቦናውን
ምድርና ፀሃይ እና ጨረቃን ጎልተው ቢታዩ
እኔ እልቃለው ሰርቶኛል እድርጎ ልዩ
የእድሜአችንን ልክ ስፍሩን ላናውቅ የነገን እጣ
ከመልካምነት ምን የተሻለ ነገር ሊመጣ
የትም ብትሆን የትም ቦታ
ተስማምተህ ኑር ይላል ቃሉ አንድ ጌታ
የትም ብትሄድ የትም ቦታ
በፍቅር ኑር ይላል ቃሉ አንድ ጌታ
እሰይ እንኩዋን
እንኩዋን ራሴን ሆንኩኝ ከምንም በላይ
ባምሳል የፈጠረኝ ለዚ አይደለል ወይ
ደስተኛ ሰው ነኝ በዘመኔ
ያሴን በመሆኔ
አልቃጣም ሌላውን ልመስል ያልሰጥኝን ይመስል
ሰው ሆይ ብዙም ሳትረበሽ
ብዙም ሳታፍር ሳትኮራ ቅድሚያ ተግባባ ከነፍስህ
ታረቅ ካንተ ነትህ ጋራ
አላነጻጽርም ራሴን ከሌላው
የኔ ያልሆነው ጠግቤ ላልበላው
በሰፈሩት ቁና መሰፈር እለ እና
ሰው ሰውን በድሎ መቼም አይል ገና
ምድርና ፀሃይ እና ጨረቃን ጎልተው ቢታዩ
እኔ እልቃለው ሰርቶኛል እድርጎ ልዩ
የእድሜአችንን ልክ ስፍሩን ላናውቅ የነገን እጣ
ከመልካምነት ምን የተሻለ ነገር ሊመጣ
የትም ብትሆን የትም ቦታ
ተስማምተህ ኑር ይላል ቃሉ አንድ ጌታ
የትም ብትሄድ የትም ቦታ
በፍቅር ኑር ይላል ቃሉ አንድ ጌታ
የትም ብትሆን የትም ቦታ
ተስማምተህ ኑር ይላል ቃሉ አንድ ጌታ
የትም ብትሄድ የትም ቦታ
በፍቅር ኑር ይላል ቃሉ አንድ ጌታ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists