Kishore Kumar Hits

Girma Tefera Kassa - Yeteferaremnew lyrics

Artist: Girma Tefera Kassa

album: Gin Yet Hager


ገና ከማለዳ ገና ከጠዋቱ
ከላይ ተወስኖ ሲላክ ወረቀቱ
በቃልኪዳን ብእር የተፈራረምነው
የአብሮነታችን ፍቅር የሰነቅነው
ያኔ ነው ያኔ ነው
በምድር ሳይበሰር የልደታችን ቀን
ከፈጣሪ በቀር አንድም ሰው ሳያውቀን
ወደ አለም ሳንመጣ ተዋደን በስጋ
ተቆራኝተን ነበር በመንፈስ እሱጋ
ትዝ ይልሻል ወይ ያን እለት
ስንገናኝ በድንገት እንደዘበት
አስበናል ወይ አልመናል
ይሄን ሁሉ አስቀድመን
እንደምንኖር ተጣጥመን
ትዝ ይልሻል ወይ ያን እለት
ስንገናኝ በድንገት እንደዘበት
አስበናል ወይ አልመናል
ይሄን ሁሉ አስቀድመን
እንደምንኖር ተጣጥመን
ገና ከማለዳ ገና ከጠዋቱ
ከላይ ተወስኖ ሲላክ ወረቀቱ
በቃልኪዳን ብእር የተፈራረምነው
የአብሮነታችን ፍቅር የሰነቅነው
ያኔ ነው ያኔ ነው
የለ ምንም ቀመር ትርፍ ስሌት ሂሳብ
በፍቅር ሃይል ብቻ እንዲ ስንሳሳብ
በአእምሮ ተግባብተን በአካል ስንጣጣም
ከምነግርሽ በላይ ደስ ብሎኛል በጣም
ትዝ ይልሻል ወይ ያን እለት
ስንገናኝ በድንገት እንደዘበት
አስበናል ወይ አልመናል
ይሄን ሁሉ አስቀድመን
እንደምንኖር ተጣጥመን
ትዝ ይልሻል ወይ ያን እለት
ስንገናኝ በድንገት እንደዘበት
አስበናል ወይ አልመናል
ይሄን ሁሉ አስቀድመን
እንደምንኖር ተጣጥመን
ትዝ ይልሻል ወይ ያን እለት
ስንገናኝ በድንገት እንደዘበት
አስበናል ወይ አልመናል
ይሄን ሁሉ አስቀድመን
እንደምንኖር ተጣጥመን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists