Girma Tefera Kassa - Meadelie lyrics
Artist:
Girma Tefera Kassa
album: Ethiopian Contemporary Music: Ene Aydelehum
አይተዉም
ለሷ ሚጠቅመዉን አምላክ ያዉቃልና
መድኢሌ እኔ ከሞከርኩት የእርሱ በለጠና
ባክነህ አትቅር ሲለዉ ለጎኔ
አዙሮ አመጣሽ አረገሽ የእኔ
ደግ ነዉ እሱ ማንም አይወቅሰዉ
ከሰዉም በላይ ያስባል ለሰዉ
እንደሰዉ እንደሰዉ
እንደሰዉ እኔም እንደሰዉ
አማረብኝ ፍቅር አየሁ
ወግ ደረሰኝ እኔም እንደሰዉ
ሰዉ ባልሆንኩኝ ባላሰብኩት ከቶ
አላገኝሽ እግሬን ካንቺ መርቶ
ባይደግፈኝ የእኔን ሩጫ ገቶ
በመንገዴ እሱ ጣልቃ ገብቶ
እኔ ሳላዉቅ አጉል ስፍጨረጨር
አንቺን ለእኔ እያበጀሽ ነበር
ዋስትናዬን የማምሻዬን ጀምበር
መሆንሽን አልጠበኩም ነበር
አልጠበኩም አልጠበኩም
ሰዉ ወድጄ እኔም እንደዉ
ያምርብኛል ብዬ አረኩት
ወግ ደረሰኝ እኔም እንደሰዉ
♪
አይተዉም
ለሷ ሚጠቅመዉን አምላክ ያዉቃልና
መድኢሌ እኔ ከሞከርኩት የእርሱ በለጠና
ባክነህ አትቅር ሲለዉ ለጎኔ
አዙሮ አመጣሽ አረገሽ የእኔ
ደግ ነዉ እሱ ማንም አይወቅሰዉ
ከሰዉም በላይ ያስባል ለሰዉ
እንደሰዉ እንደሰዉ
እንደሰዉ እኔም እንደሰዉ
አማረብኝ ፍቅር አየሁ
ወግ ደረሰኝ እኔም እንደሰዉ
♪
ከአሁን ወዲህ ስላለኝ ወዳጅ
ሳይናፍቀኝ ሳላይ ወደደጅ
ለአንቺ ልኖር ቤቴን ሳደራጅ
ቃል ገባለሁ አይግደለኝ እንጂ
በአንድ ጐጆ አድሬ መዋሌ
ደስ ብሎኛል አርጌሽ የግሌ
ከአንቺ ጋራ የቀረዉ ዘመኔ
መወሰኔ የ አርባ ቀን እድሌ
መታደሌ መታደሌ
መወሰኔ የ አርባ ቀን እድሌ
ከምወዳት ከምትወደኝ
ይዣት ልኑር ይዛኝ እንደአመሌ
እንደሰዉ እንደሰዉ
እንደሰዉ እኔም እንደሰዉ
አማረብኝ ፍቅር አየሁ
ወግ ደረሰኝ እኔም እንደሰዉ
እንደሰዉ እንደሰዉ
እንደሰዉ እኔም እንደሰዉ
አማረብኝ ፍቅር አየሁ
ወግ ደረሰኝ እኔም እንደሰዉ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist