Kishore Kumar Hits

Samon Zemas - Addis Abeba lyrics

Artist: Samon Zemas

album: Lewt


እውነት መዋደድን የአንድነት ኑሮ
ውብ ባንቺ ጥላ ስር ፍቅርን ተምሮ
ተወልዶ አድጎብሽ አይ አንቺን አውቆ
ልቡን ያስቀድማል አያይም እርቆ
የፍቅር ቤቴ ደግነት ምድረ አራዳ አዱ ገነት
አትለይም የኔ ነው አታውቅም
እላይ ታች ነች ሁሉንም
የአብሮ መኖር የፍቅር ትርጉም
አንድ ነበር ሳይኖር ህጉም
እያለፈ ክፉም ደጉም
በረከትን ስናይ እርጉም
ሞክር አምልጥ ከድህነት
አታመንታ አንዱን ምረጥ
አስተምራ መኖር መስራት
ሰታ እድል ውሃ እና እሳት
አዎ በል ንገራት እንደሆነች የሁሉም እናት
አታረጅም ገና ዉብ ናት
ዛሬም አዲስ አበባ ናት
ባህሏ አንድ ነው የምናውቃት
ፍቅርን አዲስ እሚያኖራት
ከአይኗ ብርቅ እኔ አልረሳት
ነዳ አለም ብትሆን እሳት
አዲስ አዲስ እንዳንቺስ የለም አዲስ
አዲስ አዲስ እንዳንቺስ የለም አዲስ
ዜማው ቢያንስብሽም ፅፌ ምችለው
ፍቅሬን ልግለፅልሽ እጅ መንሻዬ ይኸው
ባይሞላልኝ እንጂ ከአይንሽ የምርቀው
ወላጅ እናቴ ነሽ ሁሌም ልቤ ያንቺው ነው
ስሸኘኝ ሽቅብ አይታ በአይኖⶩ እምባ ሞልታ
አለም ክፉ ወሰደችኝ ህይወት ጨካኝ አረገችኝ
እንደ አንቺ አይደል እዛ ሄጄ ለዩኝ እኔን ቀይ ደምቼ
ዘረኝነት ክፉ ደዌ ትላንት ያዘኝ ነገን ሆኜ
ጊዜ አልፎ ተቀይሮ ናፍቆትሽ አመጣኝ ዞሮ
ቦታ አራዳው እንደ ድሮ ባይገኝም ተበትኖ
ልብ ቦታ አደለም ምሳሌ ናት አዲስ ለአለም
ካስተዋልን ትልቅ ሚስጥር
የአዲስ ሰው ሰው ነው ፍቅር
ባህሉ አንድ ነው የምናውቃት
ፍቅርን አዲስ እሚያኖራት
ከአይኗ ብርቅ እኔ አልረሳት
ነዳ አለም ብትሆን እሳት
አዲስ አዲስ እንዳንቺስ የለም አዲስ
አዲስ አዲስ እንዳንቺስ የለም አዲስ
ፈካ አበባ ወጣት ይረግፋል በዘመን
ትላንት አልፎ ትውልድ ተተካን አብበን
የሚያምረውን ህይወት የሸገርን ወርሰን
ዛሬም እንኖራለን ፍቅርን አግዝፈን
ያደግንባት ውብ እናት ፍቅር
እይ ልጆⶩን ሌላው ይቅር
ጨዋታውን እሷ ወልዳ
ባዳ የለም በሷ ሜዳ
መኖር በመሃል በህይወት በሞት
ንግድ ቁማር ሲያገኝ ነጥቆት
ሲያሳልፍ ለአምላክ ሰቶት
በቀል ክፋት ሁሉን ትቶት
ምንም ቢለያይ ኑሮ በአዲስ
እዚ አና እዛ ቢሆንም ኪስ
ሁሉ ይሞላል ፍቅር ካለ
እሱ ያያል ከላይ አለ
አዎ ማንም መጣ
ተቀብላ ፍቅር ሰጥታ
ተመቸችው ቀረ ከሷ
አይገኝም ልክ እንደሷ
ባህሉ አንድ ነው የምናውቃት
ፍቅርን አዲስ እሚያኖራት
ከአይኗ ብርቅ እኔ አልረሳት
ነዳ አለም ብትሆን እሳት
አዲስ አዲስ እንዳንቺስ የለም አዲስ
አዲስ አዲስ እንዳንቺስ የለም አዲስ
አዲስ አዲስ እንዳንቺስ የለም አዲስ
አዲስ አዲስ እንዳንቺስ የለም አዲስ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists