Kishore Kumar Hits

Samon Zemas - Fikir Neber lyrics

Artist: Samon Zemas

album: Lewt


ፍቅር ነበር የጎደለው የኔን ህይወት
ደስታ ሞላኝ ሃሴት አረኩኝ የእውነት
ፍቅር ነበር የጎደለው የኔን ህይወት
ደስታ ሞላኝ ሃሴት አረኩኝ የእውነት
ያ ንፁህ ልብሽ አሽከርክሮ ፍቅርን ወርውሮ
ከልቤ ደጃፍ ስር አሳርፎ ጥሎ
ተነቅሰሽ ለዘላለም ጨልሞም ሲነጋ
እንደዛ ነው ፍቅር ለካ ከነፍስ ሲገባ
ያኔ ሳናግርሽ የመጀመሪያ ቀን
ፈዝዤ ባይኖችሽ ስቀር እኔም አንቺም ስቀን
ተረዳሺኝ አዎ የልቤን አንብበሽ
ፃፍኩኝ ልዩ ግጥም በህይወቴ ገብተሸ
አይኖችሽ ጥበብ ልዩ ኮከብ የሚመስሉት
ነገን እያሳዩ ደስታ አስማት የሚሰሩት
ቁንጅናሽ ተዓምር ነው ልቤን አሸንፏል
ያስገርማል ስብዕናሽ ዉብ ፀባይ ሰቶሻል
አለሜን ባንቺ የፍቅር ቀለም በአዲስ ብራናዬ
ስዬ እያየሁሽ ስሚው ድምፅ አለው ደስታዬ
ፈገግታሽ የሚያምረው አዎ እያበራ ሁሉን
ባዶ የኔን ህይወት ሞላ ጎዶሎውን
ፍቅር ነበር የጎደለው የኔን ህይወት
ደስታ ሞላኝ ሃሴት አደረኩኝ የእውነት
ፍቅር ነበር የጎደለው የኔን ህይወት
ደስታ ሞላኝ ሃሴት አደረኩኝ የእውነት
ሲጨላልም አላማዬ ተስፋ እንዳልቆርጥበት
አበራሺው የኔን ህይወት ብርሃን ሆነሽለት
እየቆጠርሽ መልካም ብቻ ከዛ ሁሉ ስህተት
አደረሽው ፍቅራችንን ዛሬ ላለንበት
ዞር ብዬ ሳስተውለው ያለፍነውን እሳት
ነበር ባንቺ ትዕግስት አዎ ነበር ባንቺ ብርታት
እውነት ነው ሳልሳሳ ሁሉን የምሰጣት
አንቺ ነሽ ልዕልቷ አዎ በልቤ የማነግሳት
አዎ አንቺ ነሽ ልዩ ሌላ ማንም የለም
የሚረዳ ህልሜን የኔን ያበደ አለም
እንደዛሬ ሳይሆን ሳንደርስ ብቻችንን ሆነን
ትይኝ ነበር አምነሽብኝ ይመጣል ያንተም ቀን
ይገርመኛል ሳስታውሰው አብረን ያለፍነውን
እጓጓለው ደሞ ሳስብ ነገ የምናየውን
የአምላክ ስጦታ ነሽ የመኖሬ ምክንያት
የልቤ ባለቤት አዎ ቆንጆዋ ሽልማት
ፍቅር ነበር የጎደለው የኔን ህይወት
ደስታ ሞላኝ ሃሴት አረኩኝ የእውነት
ፍቅር ነበር የጎደለው የኔን ህይወት
ደስታ ሞላኝ ሃሴት አረኩኝ የእውነት
እንዳትርቂኝ
እንዳጠፊ
እንዳትርቂኝ

እንዳጠፊ
በፍለጋ በጥያቄ ሳስስ ነበር
እውነተኛ የልብ እረፍት ሆኖኝ ሚስጥር
ያሳደድኩት ሲያጠፋኝ የአለም ምክር
አግኝቻለው እኔ ራሴን ባንቺ ፍቅር
በፍለጋ በጥያቄ ሳስስ ነበር
እውነተኛ የልብ እረፍት ሆኖኝ ሚስጥር
ያሳደድኩት ሲያጠፋኝ የአለም ምክር
አግኝቻለው እኔ ራሴን ባንቺ ፍቅር
እረፍቴ ነው ያንቺ ፍቅር
ነው ድብቅ የደስታዬ ሚስጥር
ልቤ ውስጥ አትወጪም ነሽ ከኔ ጋር
ቢከፋም መሸም ነጋ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists