Kishore Kumar Hits

Samon Zemas - Amesgnalehu lyrics

Artist: Samon Zemas

album: Lewt


ክፉሽን አልየው እማ
እናትነት ትግስት መስዋትነት
የእውነተኛ ፍቅር ጥጉ ሚታይበት
ስለ እናት ተገልፆ አያቅም ኧረ በኔ አንደበት
ለልጆቹዋ ያላት ርህራሄ ስስት
ምትክ የላት እናትስ እናት ናት
በጋ ሆነ ክረምት ብርሀን ሆነ ለሊት
በመከራ ችግር በሀዘን ስመታ
ታበረታኛለች ቃልሽ ልቤ ገብታ
ስወድቅ የምትይኝ ተስፋ አትቁረጥ በርታ
የኔ ይቅር አንተ ኑር አንተ ነህ የኔ ደስታ
አለም ስታስከፋኝ በህይወት ስከሰስ
ካሰብኩት ካለምኩት ሲያቅተኝ መድረስ
ስብርብር እንክትክት አላማዬ ሲወድቅ
አለኝ ያልኩት ያ ተስፋ ሲጠፋብኝ ሲርቅ
ባንቺ ህይወት ካስተማርሽኝ ትግስትን ልቤ እንድያውቅ
መከራውን አሳለፍኩት ምክርሽ ሆኖኝ ስንቅ
ሀሳብሽን ባልሞላ ህልሜን ባልሆንልሽ
ቁም ነገር ባልደርስበት ማረግ ባላሳይሽ
ሁሉም ቢለዋወጥ አንቺ ለኔ አንድ ነሽ እናቴ አደለሽ?
ከአውሬው ማምለጫ መደበቂያዬ ነሽ እማ መደበቂያ ነሽ
ክፉሽን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
ክፉሽን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
ክፉሽን አልየው እማ እንባሽን አልየው እማ ተይ
ክፉሽን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
እንባሽን አልየው እማ ተይ, 4x
በፈለግሽኝ ሰዓት ባልደርስልሽ ያኔ
ሙሉ ህይወትሽን ዋጋ ከፍለሽ ለኔ
በቀን ማታ አይ ስንቱን አየሽው
ያን ሁሉ መከራ እናት እንዴት ቻልሽው
የሰው ፊት ጅራፉን ለኔ ተገረፍሽው
በጨለማ ኖረሽ ልቤን ብርሃን ሞላሽው
ጉዞ ጀምሪአለው ብቻ አንቺን አይክፋሽ
መድረሴ አይቀርም እማ ተስፋ አልቆርጥም ጭራሽ
አዎ እማ ላንቺ እጨነቃለው
እንደሆንሺልኝ ልሆን እንከራተታለው
እዚም እዛ ይኸው እሮጣለው
መንገዴ ረዘመ ደስታሽ የኔ አለም ነው
ሰው አውሬ ሆኗል አልችል ብያለው
ምክንያቱም ፍቅርን ካንቺ ተምሪያለው
ርህራሄ ደግነትን ካንቺ ወርሻለው
ግን አላዝንም ዛሬም በልቤ አይሻለው
ይሳካል ሀሳብሽ እማ ፀሎትሽ ዋጋ አለው
ሰላሙን ያብዛልሽ መቼም ክፉሽን እንየው
ሳቅሽ ለኔ እረፍት ደስታሽ ህይወቴ ነው
ከፍዬ አልጨርሰው እማ ውለታሽ ብዙ ነው
ምስጋናዬን ተቀበይኝ እማ እወድሻለው እማ እወድሻለው
ክፉሽን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
ክፉሽን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
ክፉሽን አልየው እማ እንባሽን አልየው እማ ተይ
ክፉሽን አልየው እማ ተይ እንባሽን አልየው እማ
እንባሽን አልየው እማ ተይ, 4x
ክብሬ ማንነቴ ነሽ እናቴ
ጀምሬም ባልጨርሰው
ስምሽን ላወድሰው
ገነት ላንቺ ለምድር
ሳመሰግን ለ አምላክ ስራ
እድሜ ሰቶ እንዲያሳይሽ
ታናሽ ታላቅ እንደ ህልም ሲሆንልሽ
ያ ምርቃት የማልረሳው
ልቤን ሲወድቅ የሚያነሳው
አደረሰኝ ከደጃፉ
በፀሎትሽ ከ ፅሁፉ
...ታሪክ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists