Kishore Kumar Hits

Samon Zemas - Yemechereshaw Ken lyrics

Artist: Samon Zemas

album: Lewt


ካበቃ ሆኖ መጨረሻ አዎ ሀይል የለም ጊዜን መመለሻ

ትዝታ በመጨረሻው ቀን በፍቅር እንለያይ ስቀን
ካበቃ ሆኖ መጨረሻ አዎ ሀይል የለም ጊዜን መመለሻ
ትዝታ በመጨረሻው ቀን በፍቅር እንለያይ ስቀን
ተላንት እንደ ትላንት ደስታ እና ሀዘን አለው
በትንሿ ይህወቴ ስንቱን አይቻለው
እውነቱን ተናገር ልቤ ያለው ልክ ነው
በመሸበት እደር ሁሉም ግዜያዊ ነው
ቤት የእግዚአብሔር ነው እኔ ቤት የለኝ
የአባቴ ፀሎት ካድር ባይለየኝ
እኔ ማነኝ ውስጤ ሲጠይቀኝ
ከየት ነኝ ወዴት ነኝ አዋቂ የፈጠረኝ
አልፈነው ያን ሁሉ ፈተና
አርፍደን እያልን ነው ገና
ሲጥለን ቀን ዛሬ ደርሶ
ላይመጣ እድል ተመልሶ
አይተነው መልካሙን መጥፎንም
ዞረናል ህይወት ሙሉ አለምን
አውቀነው አንብበን ሁሉንም
አሁን ላይ እውነት መልስ የለንም
ካበቃ ሆኖ መጨረሻ አዎ ሀይል የለም ጊዜን መመለሻ
ትዝታ በመጨረሻው ቀን በፍቅር እንለያይ ስቀን
ካበቃ ሆኖ መጨረሻ አዎ ሀይል የለም ጊዜን መመለሻ
ትዝታ በመጨረሻው ቀን በፍቅር እንለያይ ስቀን
ውድድር ውስጥ ገባ ሰው እኔን ብቻ አለ
ተፈጥሮን አስነባ እራሱን በደለ
በደል ደም ይወዳል ይቅርን ካልተማረ
ያላየነው የለም ግን ማን ያየን አለ
አዳራሹ ሰፊ መግቢያው ጠበባቸው
በተራ በተራ ምነው መግባታቸው
የሚያስፈልገንን ፈጥሮልን ውስጣችን
ፍልጋችን እርቆ ባከነ ህይወታችን
አልፈነው ያን ሁሉ ፈተና
አርፍደን እያልን ነው ገና
ሲጥለን ቀን ዛሬ ደርሶ
ላይመጣ እድል ተመልሶ
አይተነው መልካሙን መጥፎንም
ዞረናል ህይወት ሙሉ አለምን
አውቀነው አንብበን ሁሉንም
አሁን ላይ እውነት መልስ የለንም
ካበቃ ሆኖ መጨረሻ አዎ ሀይል የለም ጊዜን መመለሻ
ትዝታ በመጨረሻው ቀን በፍቅር እንለያይ ስቀን
ካበቃ ሆኖ መጨረሻ አዎ ሀይል የለም ጊዜን መመለሻ
ትዝታ በመጨረሻው ቀን በፍቅር እንለያይ ስቀን
ማን አለ ሲኖር ያላዘነ (ሲኖር ያላዘነ)
ቆይ ማንው ስኬትያላደነ (ማነው)
ያጣውም ያገኘ የልቡን
አንድ ነው ሲጨርስ መንገዱን (ሆኗል ይሁን)
ካበቃ ሆኖ መጨረሻ አዎ ሀይል የለም ጊዜን መመለሻ
ትዝታ በመጨረሻው ቀን በፍቅር እንለያይ ስቀን
ካበቃ ሆኖ መጨረሻ አዎ ሀይል የለም ጊዜን መመለሻ
ትዝታ በመጨረሻው ቀን በፍቅር እንለያይ ስቀን
ካበቃ ሆኖ መጨረሻ አዎ ሀይል የለም ጊዜን መመለሻ
ትዝታ በመጨረሻው ቀን በፍቅር እንለያይ ስቀን
ካበቃ ሆኖ መጨረሻ አዎ ሀይል የለም ጊዜን መመለሻ
ትዝታ በመጨረሻው ቀን በፍቅር እንለያይ ስቀን
ኖረናል በልዩነት መርጠን
ህይወትን በደረጃ ከፍልን
በጊዜ ሁሉም ለሚቀየር
ከራሱ ከመቀየር በቀር

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists