Kishore Kumar Hits

Lastarock - Aymelesem lyrics

Artist: Lastarock

album: Aymelesem (Ep)Album


አይመለስም አፍሮ አይመለስም
አይረታም አፍሮ አይሸነፍም
አይመለስም አፍሮ አይመለስም
አይሸሽም አፍሮ አያቆምም
ሰንሰለት ቀንበር ትከሻየ ላይ
ሊያደርጉኝ ሎሌ
ተምነው በብር ሊገዙ ኩራቴን
እምነት ክብር እና ስሜን
ገብተው እኔውስጥ ሊቆጣጠሩኝ
ሊያስቡ በእኔ
ሚያውቁኝ መስሏቸው ሰጡኝ ለ ክተው
ህልሜን አላማ ግቤን
አለት ተቀርጿል በሥሜ
እሳት በደሜ ውስጥ አለ ወኔ
ጥቁር ቆዳ መራር ነው ሀሞቴ
ያለኝ አቅም ወደር የለው ጉልበቴ
አልመለሥ ወደ ኋላ ልበሙሉ ምንም አልፈራ
ሞት ወይ መሆን አንድ ምርጫ
ወደፊት ነው የለኝ መውጫ
የሩቅ ኮኮብ ነኝ መንገደኛ
የተመረጥኩ እንዳበራ
አጭር መንገድ የለም በሂወቴ
ማራቶን ነው ሩጫዬ
አይመለስም አፍሮ አይመለስም
አይረታም አፍሮ አይሸነፍም
አይመለስም አፍሮ አይመለስም
አይሸሽም አፍሮ አያቆምም
ቁም ቁም ይሉኛል ቁም
ልክ አይደለህም መስመሩ ይህ ነው
ማለፍ አትችልም
ከነሱ ወዲያ ሌላ አለም የልም
እንደታሰሩ ማየት አይችሉም
በምክንያት ነው የምራመደው
ለሰው ሥል አላደርግ ለሰው ሥል አልተወው
ለማሸነፍ ነው የምሮጠዉ
አስር ሞት ቢመጣ አንዱን ግባ በለዉ
(አይመለስም
ወርቅ ነዉ ልቤ
(አይመለስም
እሳት የፈተነው
(አይሸነፍም
አሁን ወይ መቼም
(አይሸነፍም
ጊዜዉ የኔነዉ
(አይመለስም
ጀግና አልጠብቅም
(አይመለስም
ሂወቴን አንዲያድነዉ
(አይሸነፍም
እሥትንፋሴ እስኪያቆም
(አይሸነፍም
እፋለማለው
አይመለስም አፍሮ አይመለስም
አይረታም አፍሮ አይሸነፍም
አይመለስም አፍሮ አይመለስም
አይሸሽም አፍሮ አያቆምም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists