Kishore Kumar Hits

Lastarock - Ewen Yihonal lyrics

Artist: Lastarock

album: Ewen Yihonal


ትለኝ ነበረ ተነስ ልጄ
ይጠንክር ልብህ አይድከም ተሎ
መች ይዘለቃል ተስፋ ተቆርጦ
በዚ ዓለም ኑሮ እጅ ተሰቶ
ስደስት ጊዜ ወድቆ ያዩት
አትችልም አይሆንም ያሉት
ትልቁን ዜማ ተቀኘው በሰባተኛው ሰዓት
አለቺኝ እማማ ፈልጋት ያቺን ዉብ ዜማ
ሁሌ በተስፋ ቁም አይቀርም ህልም እዉን ይሆናል
ገና ሂወትን እኔስ መቼ ጀምሬው
አልሆነልኝ ብዬ ተስፋ የምቆርጠው
አንዱ በር ቢዘጋ ሌላው ይከፈታል
በተስፋ ቁሚአለው ህልሜ እዉን ይሆናል
አለቺኝ በል ልጄ ጠንክረህ ስራ ከልበህ
እይ ወደላይ ሲከብድህ የልብህን አይቶ እንዲሞላለህ
ማይቻል የለም ካመንክ በራስህ
አትጠራጠር ታሸንፋለህ
በል አሳያቸው መንገዱን አልፈህ
ይዎድቃል ብለው ለሚጠብቁህ
ቢያስከፍለኝ ትልቅ ዋጋ
ህልሜን ልኖር ሁሉን ባጣ
ምንም ቢሆን ዝግጁ ነኝ
ካሰብኩት ሳልደርስ እንቅልፍ አይኖረኝም
በድል አላምን የለኝ ጊዜ
ቀንም ማታም እሮጣለው
ሁሌም ትልቅ ነው ማስበው ደከምኩ አልልም እስክጨርሰው
ገና ሂወትን እኔስ መቼ ጀምሬው
አልሆነልኝ ብዬ ተስፋ የምቆርጠው
አንዱ በር ቢዘጋ ሌላው ይከፈታል
በተስፋ ቁሚአለው ህልሜ እዉን ይሆናል

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists