Kishore Kumar Hits

Endale Woldegiorgis - Denq Neh lyrics

Artist: Endale Woldegiorgis

album: Zelalemawi


ድንቅ ፡ ነህ (Denq Neh)
ጌታ ፡ ፈጣሪዬ ፡ ስለ ፡ አፈጣጠሬ
ስለሚያስደንቀው ፡ ስለ ፡ አካል ፡ ክፍሌ
ላመሰግንህ ፡ እፈልጋለው
ግሩም ፡ ድንቅ ፡ ሆኜ ፡ ተፈጥሪያለው ፪X
ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ
ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ ፪X
የማመስገኛ ፡ ምክንያት ፡ ከሆነ
ከቁጥር ፡ በላይ ፡ እኔ ፡ ጋር ፡ አለ
እግሬ ፡ ሲራመድ ፡ ሚዛን ፡ ጠብቆ
ዓይኔም ፡ ሲያይልኝ ፡ ቅርብም ፡ አርቆ
በራስ ፡ ቅሌ ፡ ላይ ፡ ሲበቅል ፡ ፀጉሬ
ጣቶቼ ፡ ላይ ፡ ሲያድግ ፡ ጥፍሬ
ውበት ፡ አላቸው ፡ በየቦታቸው
ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሰራሃቸው ፪X
ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ
ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ ፪X
ሰው ፡ ሰውን ፡ ቢሰራው
ቢያበጀው ፡ እስትንፋስ ፡ ቢሰጠው
የሚከፍለው ፡ አጥቶ
ሁሉም ፡ ሰው ፡ መኖር ፡ በተሳነው
ይተመን ፡ ቢባል ፡ በዋጋ ፡ የአካል ፡ ክፍሌ
በዓለም ፡ ያለው ፡ ሃብት ፡ በሙሉ ፡ አይመጥን ፡ ለኔ
እንዃን ፡ ሁሉንም ፡ ይቅርና ፡ አንዱንስ ፡ እንኳ
መፍጠር ፡ ያልቻለው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ እንዴት ፡ ይመካ
ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ
ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ ፪X
በሚጥም ፡ ዜማ ፡ የሚያዜመው ፡ የአንተን ፡ ዝማሬ
ገንዘብ ፡ ሊገዛው ፡ አይችል ፡ ይህ ፡ አንደበቴ ፪X
ጌታ ፡ ፈጣሪዬ ፡ ስለ ፡ አፈጣጠሬ
ስለሚያስደንቀው ፡ ስለ ፡ አካል ፡ ክፍሌ
ላመሰግንህ ፡ እፈልጋለው
ግሩም ፡ ድንቅ ፡ ሆኜ ፡ ተፈጥሪያለው ፪X
ግሩም ፡ ነህ ፡ የሰራሀኝ
ድንቅ ፡ ነህ ፡ የፈጠርከኝ ፪X

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists